የሰዎች ራስ ወዳድ {‘Selfish’} መሆን ሁልጊዜ ከመጥፎ ማንነት አይመጣም፤ አብዛኛውን ጊዜ ከተሰበረ ደግነት የሚወለድ መከላከያ (Defense mechanism) ነው !🙌
በሕይወታችሁ ውስጥ ለሁሉም ሰው ድልድይ ለመሆን አትሯሯጡ። ደግነታችሁንና ቅንነታችሁን አላግባብ የሚጠቀሙ ሰዎች፣ መጨረሻ ላይ እናንተን ሰብረው ያላችሁን መልካምነት ይገድሉታል፦
ለሁሉም ሰው ሲባል ራስን መስዋዕት ማድረግ… ደግነት ሳይሆን የራስን ማንነት ማጣት ነው።
እናንተ ለረዳችኋቸው ሰዎች ሁሉ… በችግራችሁ ሰዓት ከጎናችሁ እንዲቆሙ አትጠብቁ ፤ አብዛኞቹ ሰዎች ዋጋችሁን የሚያውቁት ስታጡላቸው ብቻ ነው።🙌
ሰዎችን ለመርዳት ስትሉ የራሳችሁን የአዕምሮ ሥላም {Mental health} አሳልፋችሁ አትስጡ። ለራሳችሁ ወሰን (Boundary) ማበጀታችሁና እንቢ ማለታችሁ ራስ ወዳድነት ሳይሆን ራሳችሁን የመጠበቅ ብልህነት ነው።
አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ‘ራስ ወዳድ’ የሚሏቸው ግለሰቦች፣ ትላንት ለሁሉም ሰው ሲሉ ራሳቸውን የሰጡና ደግነታቸው በአስመሳይነት የተመለሰላቸው ናቸው።💔
ደግ መሆን ውብ ስብዕና ነው ፤ ነገር ግን ደግነታችሁ ወሰን (Boundary) ከሌለው ሰዎችን ሳይሆን እናንተን ያፈርሳል። ለራሳችሁ ሰላምና አእምሮአችሁ ቅድሚያ መስጠት ራስ ወዳድ {‘Selfish’} መሆን አይደለም።
ለሚገባው ሰው ብቻ መስጠትንና ለሠላማችሁ ሲባል ‘እንቢ’ ማለትን ልመዱ። 🤍✨
በርቱ ! አመሰግናለሁ !
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇🏽👇🏽👇🏽
t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇🏽👇🏽👇🏽
Fb.com/danelroza
ለኢንስታግራም
👇🏽👇🏽👇🏽
Instagram.com/danelroziye
Subscribe to get the latest posts sent to your email.
