7 Oct 2026, Wed

የ2 ደቂቃ ሕግ ቀላል የሥራ አመራር መርህ ነው።

አንድ ሥራ ከ2 ደቂቃ በታች የሚወስድ ከሆነ፣ ለወደፊት አታስተላልፉት፤ ወዲያውኑ አድርጉት!

የዚህ ሕግ ጥቅሙ!

✔️ ትንንሽ ሥራዎች እንዳይከማቹ ይከላከላል

✔️ ትንንሽ ሥራዎችን እያስተላለፍን ስናዘገያቸው፣ በመጨረሻ ብዙ ሥራ ይሆናሉ።

✔️ የአእምሮ ጫናን ይቀንሳል

✔️ ያልተጠናቀቁ ትንንሽ ሥራዎች በአእምሮአችን ቦታ ይይዛሉ። ወዲያውኑ ማጠናቀቃቸው ነፃ ያደርገናል።

✔️ የእርምጃ ልምድን ይገነባል

✔️ “በኋላ አደርገዋለሁ” ከማለት ይልቅ “አሁን አደርገዋለሁ” የሚል አመለካከት ይገነባል።

✔️ ትልቅ ሥራ ለመጀመር ፍጥነት ይሰጣል

✔️ ትንንሽ ሥራዎችን ማጠናቀቅ ወደ ትልልቅ ሥራዎች ለመግባት ያበረታታል።

ምሳሌዎች

✔️ አስፈላጊ አጭር መልዕክት (text) መመለስ → አሁኑኑ መመለስ።

✔️ አንድ ያነሳነውን ነገር ስረችንን ከጨረስን በኋላ ወደ ቦታው መመለስ → አሁኑኑ ማድረግ።

✔️አንድ አዲስ ሃሳብ ሲመጣልን መመዝገብ → አሁኑኑ መመዝገብ።

✔️ እነዚህና መሰል ተግባሮች የሚወስዱት ጊዜ ከሁለት ደቂቃ በተች ስለሆነ ወዲያውኑ አድርገናቸው ማለፍ ስኬታማነታችንን በዛዋል፡፡

አስፈላጊ ማስታወሻ፡-

ይህ ሕግ “ከ2 ደቂቃ በታች የሆነ ሁሉንም ሥራ ሁሉ በዚያኑ ሰከንድ ማድረግ አለባችሁ” ማለት አይደለም።

ቀላል መርህ፦

“የሚፈጀው ጊዜ ከ2 ደቂቃ በታች ከሆነ እና አሁኑኑ ማድረጉ ሆኖ ዋናውን የዕለቱን ሥራ ካላስተጓጎለ አሁኑኑ አድርጉት!”


Discover more from ዳንኤል

Subscribe to get the latest posts sent to your email.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Discover more from ዳንኤል

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading