11 Jun 2026, Thu

የተሳሳተ ቁልፍ ነው የሰጠኸኝ ፤

የኦቶማን ንጉስ አህመድ ወደ ጦርነት ከመሄዱ በፊት ሚስቱን (ቆንጆዋን ንግሥት) በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎ ቁልፉን ለቅርብ ጓደኛው ሙሳ ሰጠው እና “በአራት ቀናት ውስጥ ካልተመለስኩ ክፍሉን ክፈተው እና እሷ ያንተ ነች” አለው።

ፈረሱ ላይ ወጣና ወደ ጦር ሜዳ ጋለበ። ከግማሽ ሰዓት በኋላ ንጉሱ ከኋላው ደመና የመሰለ አቧራ አየ። ቆም ብሎ ሲመለከት ጓደኛው ወደ እሱ በፍጥነት እየጋለበ ሲመጣ አየው።

“ምንድነው ችግሩ ?” ንጉሱን ጠየቀው። ሙሳም ትንፋሹ እየቆራረጠ 

“የተሳሳተ ቁልፍ ነው የሰጠኸኝ” ሲል መለሰለት።

ቁልፎቹን ከመሞከሩ በፊት ለ፬ ቀናት ይቅርና ለ፩ ሰአት እንኳን አልጠበቀም።

እንደ “ጓደኞችህ” ከምትቆጥራቸው ሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት ላይ ተጠንቀቅ።

በትጋት ለምታገኘው ሃብት አደራ ልትሰጣቸው ትችላለህ –  እነሱ ግን በቅርቡ እንድትሞት እየተመኙልህ ሊሆን ይችላልና እራስህን ከጓደኛህም ቢሆን መጠበቅህን አትዘንጋ።

ራሳችንን እንፈትሽ ፡ ራሳችንን እንመልከት።

ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇👇👇
Fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇🏾👇🏾👇🏾
linkedin.com/in/danelroz


Discover more from ዳንኤል

Subscribe to get the latest posts sent to your email.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Discover more from ዳንኤል

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading