7 Oct 2026, Wed

ሕይወትን በሙሉ ንቃት ፡ ጥበብና ዕቅድ በቆራጥነት መምራት

በህይወት የምናደርገውን ጉዞ ሳናውቀው እያዘገዩ ወደ ታች የሚጎትቱን አደገኛ አጥፊዎች አሉ፤ እነዚህንም ሰብረን ካልጣስናቸው የስኬትን ማማን መረገጥ ከንቱ ህልም ሆኖ ይቀራል። የመጀመሪያው አጥፊ መንገድ አዲስና አጓጊ በሚመስል ነገር ሁሉ እየተዘናጉ ከአንድ ሀሳብ ወደ ሌላው የመሮጥ የትኩረት መበታተን ሲሆን ይህም ጅምር እንጂ ፍጻሜ የሌላቸው ስራዎችን በማብዛት አቅምን ያከክሻል። ከዚህ በተጨማሪ ያለፈውን ድል እንደ ዘላለማዊ ዋስትና በመቁረጥ ወይም ባለፈው ትናንት ስህተት ተስፋ በመቁረጥ በታሪክ ጥላ ስር መታሰር የዛሬን እድል ይዘጋል። ሁሉንም ነገር በገዛ እጅ ብቻ ለመስራት መሞከርና እርዳታን እንደ ድክመት መቁጠርም አእምሮን ለከፍተኛ የብልሽትና የደካክማ ስሜት የሚዳርግ አደገኛ መንገድ ነው።

በሌላ በኩል ዓለምና ገበያው ሲቀየሩ አብሮ ከመዘመን ይልቅ በግትርነት አቋምን አለመልቀቅ ሰውን ጊዜው ያለፈበትና ተወዳዳሪ አልባ ያደርገዋል፤ የረጅም ጊዜ መሰረት ከመገንባት ይልቅ በአጭር ጊዜና በአቋራጭ ውጤት ለማግኘት መቸኮል ደግሞ የመጨረሻ ውድቀትን ይጋብዛል። ከዚህም በላይ አእምሮን የሚያደፈርሱና ተስፋ የሚያስቆርጡ አሉታዊ ሰዎችን ከጎን ይዞ መጓዝ የውስጥ ሰላምን ያደፈርሳል፤ ላጋጠመ ውድቀት ሁሉ ሌሎችን ተጠያቂ በማድረግ የባለቤትነት ስሜት ማጣት ደግሞ ህይወትን በራስ ቁጥጥር ስር እንዳይወድቅ ያደርጋል።

እነዚህን ሰንሰለቶች ሰብሮ መውጣት የብስለትና የለውጥ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። በአንድ ዋና ግብ ላይ ማተኮርች፣ ትናንት ማለፉን አምኖ ዛሬን በአዲስ ተስፋ መጀመር ስራዎችን ማካፈልና ጠንካራ መረብ መገንባት ለስኬት መንገድ ይከፍታል። በተጨማሪም ያለማቋረጥ በመማር ከወቅቱ ጋር መላመድ፣ ሂደቱን መውደድ፣ የቅርብ ክበብን በጥንቃቄ መምረጥና ሙሉ ሀላፊነትን በራስ መሸከም እውነተኛውን የነፃነት አየር እንድንተነፍስ ያስችለናል።
ስለሆነም በእነዚህ አጥፊ ባህሪያት እስረኛ ሆነህ እድሜህን በከንቱ ከመጨረስ ተላቀቅ። በጉዞህ ላይ የተደቀኑትን እነዚህን የውድቀት ማነቆዎች ዛሬውኑ በቆራጥነት በመበጠስ ህይወትህን በሙሉ ንቃት፣ ጥበብና እቅድ በመምራት ወደተመኘኸው የታላቅነት  ማማ በልበ ሙሉነት ተራመድ !


Discover more from ዳንኤል

Subscribe to get the latest posts sent to your email.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Discover more from ዳንኤል

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading