ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ዝም ማለት የሚሻልባቸው ሰዎች
ከዚህ በታች የተጠቀሱት ኤነት ሰዎች ሲያጋጥሟችሁ መልስ ከመስጠት ወይም ከመመላለስ ይልቅ ዝምታ ተመራጭ ነው፡፡
አስታውሱ፣ ዝምታ ድክመት አይደለም፤ አንዳንድ ጊዜ ራስን መቆጣጠርና ስሜታዊ ብልህነት ነው።
፩. ሆን ብለው እናንተን ለማበሳጨት የሚናገሯችሁ ሰዎች እንደዚህ አይነት ሰዎች የሚፈልጉት የቁጣ ምላሻችሁን ተጠቅመው ነገር ለማባባስ ስለሆነ ዝም ማለት ተመራጭ ነው።
፪. ሁልጊዜ መከራከር የሚፈልጉ ሰዎች
እንደዚህ አይነት ሰዎች ዓላማቸው እውነትን መፈለግ ሳይሆን ማሸነፍ ነው፣ ስለዚህ መከራከሩ ብዙ ጊዜ ውጤት አስለማያመጣ ዝመታ ተመራጭ ነው።
፫. በጣም መቆጣት የሚቀናቸው ሰዎች
እንደዚህ አይነት ሰዎች ምላሽ ባገኙ ቁጥር ስለሚብስባቸው እሰከሚረጋጉ ዝምታ ተመራጭ ነው፡፡
፬. የሚሰድቧችሁና የማያከብሯችሁ ሰዎች
እንደዚህ አይነት ሰዎች ብትመልሱላቸው ለመመላለስ የማይመጥናችሁን ቃላት በመናገር ሊቀጥሉ ስለሚችሉ ዝምታ ተመራጭ ነው፡፡
፭. ንግግራችሁን የሚያጣምሙ ሰዎች
እንደዚህ አይነት ሰዎች መልስ ባገኙ ቁጥር ያንን መልስ ጨምረው ወደማጣመም ስለሚሄዱ ዝምታ ተመራጭ ነው፡፡
፮. ወሬ የሚያወሩ ሰዎች
እንደዚህ አይነት ሰዎች ለወሬያቸው ምላሽ ስትሰጡ እንደተሳትፎ ስለሚቆጥሩትና ችግሩን የበለጠ ስለሚያስፋፉት ዝምታ ተመራጭ ነው፡፡
፯. አንተን ለመረዳት (ለመገንዘብ) ፈቃደኛ ያልሆኑ ሰዎች
እንደዚህ አይነት ሰዎች ሁልጊዜ ራሳችሁን ለማስረዳት ስትሞክሩ ፈቃደኛ ስለማይሆኑና ስሚያደክሟችሁ ዝምታ ተመራጭ ነው፡፡
፰. ድንበራችሁን ደጋግመው የሚያልፉ ሰዎች
እንደዚህ አይነት ሰዎች ምንም ብትነግሯቸው ከተግባራቸው ስለማይመለሱ ሁልጊዜ ከመከራከር ይልቅ ድንበራችሁን በግልጽ በማስቀመጥ ዝምታ ተመራጭ ነው፡፡
Subscribe to get the latest posts sent to your email.