7 Oct 2026, Wed

“ሕይወት እንደ በረዶ ኳስ ናት። አስፈላጊው ነገር እርጥብ በረዶ እና ረጅም ተራራ ማግኘት ነው።” ዋራን ቡፌት

የመጽሀፍ ማጠቃለያ
የመጽሐፉ ርዕስ “The Snowball” (የበረዶ ኳስ)

ይህ አባባል በሕይወት፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በሀብት ግንባታ ውስጥ ያለውን የተደራራቢ እድገት (Compounding) መርህ ያመለክታል። ትንሽ ግን ትክክለኛ የሆኑ ውሳኔዎችና ተግባራት በረጅም ጊዜ ሲደጋገሙ እጅግ ትልቅ ውጤት እንደሚያመጡ ያስተምራል።

📚የመጽሐፉ ዋና መልዕክት
የመጽሐፉ ዋና መልዕክት ታላቅ ሀብት ፣ ዘላቂ ስኬት እና ጠንካራ ስም በአንድ ጊዜ እንደማይገነቡ ነው። እነሱ የሚገነቡት በትዕግሥት ፣ በቀጣይነት በመማር ፣ ውሳኔዎችን በጥበብ በመወሰን ፣ በታማኝነት እና በተደራራቢ እድገት (Compounding) ነው። ቡፌት የሚያስተምረው ትልቁ ትምህርት ፣ “ስኬት ከአንድ ታላቅ እርምጃ አይመጣም ፤ በትንሽ ግን ትክክለኛ ውሳኔዎች በተከታታይ ይገነባል።” የሚለው ነው። ቡፌት ከሕፃንነቱ ጀምሮ ለንግድ ያለውን ፍላጎት በተግባር አሳይቷል። በልጅነቱ ማስቲካ ፣ ኮካ ኮላ እና ሌሎች ምርቶችን መሸጥ ፣ ጋዜጣ ማከፋፈል እና የተለያዩ ትንንሽ የንግድ ስራዎችን በመስራት ገቢ ያመነጭ ነበር። ይህም በወጣትነቱ ብዙ ገንዘብ እንዲያከማች እና የኢንቨስትመንት ጉዞውን ቀደም ብሎ እንዲጀምር አስችሎታል።

✍️✍️✍️በመጽሐፉ ውስጥ የሚከተሉትን 8 ዋና ዋና ሀሳቦች ይገኛሉ፦

✅1. ተደራራቢ እድገት (Compounding) ኃይል፡
ቡፌት በአጭር ጊዜ ሀብታም አልሆነም ፤ ሀብቱ የተገነባው በረጅም ጊዜ ውስጥ በተደራራቢ እድገት ነው። ከትንሽ ዕድሜ ጀምሮ ኢንቨስት በማድረግ፣ ያገኘውን ትርፍ መልሶ ኢንቨስት በማድረግ፣ትልልቅ ኪሳራዎችን በመቆጣጠር፣ በገበያ ውስጥ ለብዙ ዓመታት በትዕግሥት በመቆየት ነው። ዋናው መለእክት ጊዜ በኢንቨስትመንት ውስጥ ከገንዘብ በላይ ዋጋ ያለው ሀብት ነው።

✅2. ዋጋ ላይ ኢንቨስት ማድረግ (Value Investing)
ይህ የቡፌት የኢንቨስትመንት ፍልስፍና ነው። Value Investing (ዋጋ ላይ ኢንቨስት ማድረግ) መሠረታዊ ሃሳቡ ጥሩ ኩባንያዎችን ከእውነተኛ ዋጋቸው በታች ሲሸጡ መግዛት ነው። ቡፌት ሁልጊዜ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቁ ይላል- የዚህ ኩባንያ እውነተኛ ዋጋ ስንት ነው? ገበያው ከእውነተኛ ዋጋው በታች እየገመተው ነው? ለረጅም ጊዜ ትርፋማ መሆን ይችላል? የተሳካ ኢንቨስትመንት የፋሽን አክሲዮኖችን መከተል ሳይሆን፣ ጥሩ ንግዶችን በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት ነው።

✅3. አክሲዮን ሳይሆን ንግድ ግዙ፡
አክሲዮን ስትገዙ የኩባንያውን ንግድ እየገዛችሁ ነው። ስለዚህ ከዕለታዊ የአክሲዮን ዋጋ ይልቅ የሚከተሉትን ይመልት፦ የአስተዳደር ጥራት፣ የኩባንያው ተወዳዳሪነት፣ ትርፋማነት፣የወደፊት የእድገት እድል ተመልከቱ ይላል። ኢንቨስትመንት የኩባንያ ባለቤትነት ነው፣ የዋጋ ጨዋታ አይደለም።

✅4. የኢኮኖሚ ግንብ (Economic Moat)
ቡፌት ለተወዳዳሪዎች ለመቅዳት አስቸጋሪ የሆነውን የንግድ ጥንካሬ Economic Moat ብሎ ይጠራዋል።ምሳሌዎች፦ ጠንካራ ብራንድ፣ የደንበኛ ታማኝነት፣ ዝቅተኛ የምርት ወጪ፣ የኔትወርክ ተፅዕኖ፣ የፈጠራ መብት (Patent) ነው። በጣም ጥሩ ንግዶች ለተወዳዳሪዎች ለመቅዳት አስቸጋሪ ናቸው።

✅5. ስሜትን መቆጣጠር (Control Emotion)
ሰዎች በሚወስኑት ውሳኔ ሁሉ ስሜት አለ። ቡፌት ከብዙ ኢንቨስተሮች የሚለየው ስሜቱን በመቆጣጠሩ ነው። ከሚከተሉት ይርቃል፦ ፍርሃት፣ ስግብግብነት፣ በጭፍን ብዙሃኑን ከመከተል። በኢንቨስትመንት ላይ ስሜትን መቆጣጠር እንደ ፋይናንስ እውቀት አስፈላጊ ነው።

✅6. የችሎታ ክልል (Circle of Competence)
ንግድ እውቀት ይፈልጋል። ቡፌት የማይረዳውን ንግድ አይገዛም። ይህን Circle of Competence ብሎ ይጠራዋል። ሁሉንም ማወቅ አያስፈልግም፤ የምታውቁትን በጥልቀት ማወቅ ይበቃል።

✅7. በቀጣይነት መማር
ቡፌት የቀኑን ብዙ ክፍል በማንበብ ያሳልፋል። ከሚያነባቸው፦ ዓመታዊ ሪፖርቶች፣ የፋይናንስ መግለጫዎች፣ ጋዜጦች፣ የኢንዱስትሪ ጥናቶች፣ መጻሕፍት። እውቀትም እንደ ገንዘብ በተደራራቢ ሁኔታ ያድጋል ብሎ ያምናል።

✅8. መልካም ስምና ታማኝነት
ቡፌት እንዲህ ይላል፦ “ስም ለመገንባት 20 ዓመት ይፈጃል፤ ለማጥፋት 5 ደቂቃ ብቻ ይበቃል።” ታማኝነት በንግድ፣ በሙያ እና በሕይወት ከፍተኛ ጠቃሜታ አለው።

🟣ማጠቃለያ
The Snowball የሚያስተምረው ታላቅ ስኬት ፣ ሀብት እና ዘላቂ ተጽዕኖ ከአንድ ታላቅ ውሳኔ እንደማይመጡ ነው። ይልቁንም በትክክለኛ ውሳኔዎች ፣ በቀጣይ መማር ፣ በትዕግሥት፣ በታማኝነት እና በተደራራቢ እድገት መርህ ላይ በተመሠረተ የረጅም ጊዜ ጉዞ እንደሚገነቡ ያሳያል።

አመሰግናለሁ


ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇🏽👇🏽👇🏽
t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇🏽👇🏽👇🏽
Fb.com/danelroza
ለኢንስታግራም
👇🏽👇🏽👇🏽
Instagram.com/danelroziye


Discover more from ዳንኤል

Subscribe to get the latest posts sent to your email.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Discover more from ዳንኤል

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading