❤️ ሰዎች ቢያገሉህ ወይም ቦታ ባይሰጡህ አትዘን።
ብዙ ሰዎች ውድ ነገሮችን ባለማወቅ ይንቃሉ ፤ ርካሽ ነገሮች ላይም ይሻማሉ ፤
ሁሉም ነገር በጊዜ ሂደት ያልፋል ፤ ሁሉም ሰው በተለያዬ ሁኔታ ፣ ለተወሰነ ጊዜ በህይወትህ ይከሰታል ፤ ስለዚህ በህይወት እውነታ ተደሰት። መንገድህን ቀጥል።
😘 የተወለድከው ከድሃ ቤተሰብ ከሆነ ‘እንኳን ደስ ያለህ !’ ምክንያቱም ይሄ ቤተሰብህን በጉብዝናህ ሃብታም እንድታደርግ ፈጣሪ የሰጠህ ዕድል ነው።
ቀጣይነት ያለው ሰው ሁን ፤ ነገሮችን በጅምር አታቋርጥ ፤ ለራስህም ይሁን ለቤተሰብህ ለውጥን የምትጽፍ ልዩ ትሆናለህ።
ዋጋ ሳትከፍል ያለመሰዋትነት የምታሳካው ምንም ነገር አይኖርም ፤ መሰዋትነት ፣ ችግሮችን መጋፈጥ የህይወት አካል ስለሆነ- እመንበት።
ትክክለኛውን ነገር ለማግኘት ተገቢውን ዋጋ እስከ-ከፈልክ ጸጸት ህመም ሆኖ ሰላምህን አይነሳህም።
😍 የሰዎች መሄድ መምጣት ሳይሆን ፣ ያንተ መስራት አለመስራት ጥያቄ ሊሆንብህ ግድ ነው።
ልብ በል… አንተ ርካሽ ነገር አይደለህም ፡ አንተ ውድ ነህ !
ራሳችንን እንፈትሽ ፡ ራሳችንን እንመልከት።
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
Fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇🏾👇🏾👇🏾
linkedin.com/in/danelroz
