ስፍራ ማለት ፣ ያላችሁበት ሥራ ፣ የምትኖሩበትን ቤት ፣ ጓደኝነታችሁን ወይም ሌሎችን የወደፊታችሁ የሚወስኑ ሁታዎችን የሚወክል ጉዳይ ነው፡፡
ከተጠቀሱትና ከመሰል ሁኔታዎች አንጻር ውስጣችሁ ያመነበትን ፣ ለእናንተ ተስማሚና ትክክለኛ የሆነውን “ስፍራችሁን” ማግኘት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
ስፍራችሁን ለይታችሁ ያለማወቃችሁ ቀንደኛው አጉል ውጤት ያላችሁበትን ስፍራ ተቀብላችሁ እዚያው የመክረማችሁ ጉዳይ ነው፡፡
ይህ ሲሆን ዕድሜያችን እንዲሁ እናባክናለን ፣ በአንድ ሥፍራ ተተክላችሁ በመቅረታችሁ ምክንያት ትክክለኛና ለእናንተ መሆን የሚገባቸው ዕድሎች ያመልጠናል ፣ ውስጣችን ተስፋ ይቆርጣል . . . ፡፡
ስለዚህ ስፍራችሁን ልይታችሁ ለማወቅ ማድረግ ያለባችሁን ማድረግ አለባችሁ፡፡
ስፍራችሁን ከለያችሁ በኋላ እዚያ እስክትደርሱ ድረስ አሁን ባላችሁበት የመቆየታችሁ ሁኔታ ችግር የለበትም ፤ ስፍራችሁን ከለያችሁ በኋላ ግን አሁን ያላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ካለማቋረጥ ወደትክክለኛ ስፍራች የምትደርሱበትን ዕቅድ ማውጣት አለብን፡፡
ያንን ዕቅድ ካወጣችሁ በኋላ ደግሞ ጉዞ በመጀመር ካለማቋረጥ ወደዚያ መንቀሳቀስ የግድ ነው ፤ ይህ እንቅስቃሴ የሚያስከፍላችሁን ሁሉ መስዋዕትነት ከመክፈል ወደኋላ አንበል፡፡
ስፍራችሁን ከለያችሁ በኋላ እዚያ መድረስ ከባድና መስዋዕትነት እንደሚያስከፍላችሁ እስባችሁ ያላችሁበት ከቀራችሁ የበለጠ ዋጋ ያስከፍላችኋል፡፡
አንድ ነገር አትዘንጉ ፤ ወደ ትክክለኛው ስፍራችሁ ለመራመድ ከምትከፍሉት ዋጋ የበለጠ የምትከፍሉት ስፍራችሁ ባልሆነ ቦታ በመቆየት ነው፡፡
በመንቀሳቀስ የአጭር ጊዜ ዋጋ እንከፍላለን ፤ ያላንበት በመቅረት ግን የረጅም ጊዜ ዋጋ ትከፍላላችህ፡፡
ያላችሁበትን ስፍራ እንመርምር ፤ ትክክለኛውን ስፍራችንን እንለይ ፣ ከዚያም በጥንቃቄ ወስነን ካለንበት ወጥተን እንቀሳቀስ !
ራሳችንን እንፈትሽ ፡ ራሳችንን እንመልከት።
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
Fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇🏾👇🏾👇🏾
linkedin.com/in/danelroz
