10 Apr 2026, Fri

በመካከለኛው ዘመን በአንድ የፈረንሣይ ከተማ ውስጥ ሴቶች መርዝ በመግዛት ባላቸው በሚመገበው ቁርስ ላይ በማለዳው የመቀላቀል ባህል ነበራቸው። ባል ወደ ቤቱ ከተመለሰ በምሽቱ መጀመሪያ ላይ ፀረ-ባክቴሪያውን ወይም የመርዙን ማክሸፋ ይሰጡታል። በዚህ ምክንያት መርዙ ሰውዬውን አይጎዳውም ነበር። ግን ወደ ቤቱ ባይመለስና ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ ካደረ መድሃኒቱን ለመውሰድ ዘግይቷል ማለት ነው። ስለዚህ ባልየው በራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ በመንፈስ ጭንቀት እና በአካላዊ ህመም ይሠቃያል። ሰውዬው ከቤቱ ርቆ በሄደ ቁጥር የመርዙ ውጤት በዛው ልክ እየጠነከረ ይመጣል።

ነገር ግን ባል ወደ ቤት ሲመለስ የፈጠነ ሚስቱ ሳይነቃባት መድሃኒቱን ከምግብ ጋር ቀላቅላ ትሰጠዋለች። እናም በሚገርም ሁኔታ ​​በደቂቃዎች ውስጥ ይሻለዋል። ባልየው በሚስቱ ብልሃት ተሸውዷል። ምክንያቱም ከቤት መውጣቱ ህመም፣ ድብርት እና ማቅለሽለሽ እንደሚያመጣበት በማሰብ ከቤቱ እና ከሚስቱ ጋር ይበልጥ መጣበቅና መክረሙ የመጨረሻ አማራጩ አድርጎታል።

ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *