የፍቅር ዘፈኖችን ማዳመጥ አቁም፤ ወደ ደካማ ስሜታዊ ወንድ ይለውጥሃል!።
ስልክህ ውስጥ ያለን አሳዛኝ የዘፈን ዝርዝር በከፈትክ ቁጥር እየተፈወስክ አይደለም ይልቅ ወንድነትህን እየገደልክ ነው!።
እነዚያ ለስላሳ የፒያኖ ቁልፎች እንደመሆን ያለህ፤ በማይረቡ ቃላት መታጨቅ፤ ሴቷ በስሜት ጠምዳህ አሺሽህ ሆናለች። አዎ እንደሱሰኛ ታስረሃል። ደግሞ ከሁሉ የከፋ አንተን ተጋላጭ ያደረገ ንድፍ በዚህ አለም ላይ ተነድፎልሃል።
ሴት እድል እንድትሰጥህ መለመንህ ያለህን ዋጋ አርክሶታል። መለመን መለማመጥ ደካማ እና ለእሷ መጠቀሚያነት መጋለጥ ብቻ ነው ትርፉ። ደስታህን በሴት ፈቃደኝነት ውስጥ እንዲጸባረቅ አድርገሃል።
የምንሰማቸው የዘፈን ግጥሞች ሁሌም ተመሳሳይ ናቸው፦ “ትልቅ ጉዳዬ ነሽ ቅድሚያ የምሰጥሽ..”
በእውነት ይህ ፍቅር አይደለም፤ ይህ ራስን ማጥፋት ነው። እንደዚህ አይነት ግጥሞች አንተ የእሷ ባርያ ከማድረግ በስተቀር ዋጋ የላቸውም!።
ሴት አላማህ አይደለችም። ወይም አሻጋሪ ሙሴህ አይደለችም። አዳኝህም አይደለችም። ከአሸናፊው ጋር ጋላቢ ነች። አንተ የፍላጎቷ አድራሽ መገልገያዋ ነህ። ወዴት እንደምትሄድ ካላወቅክ ደግሞ ልንገርህ፤ ወደ አመድ ወደምትቃጠልበት ገደል እየሄድክ ነው..!።
ሴቶች ጣታቸውን በገላችን ላይ በማርመስመስ ብቻ እንደ አማልክት እንድናመልካቸው የማድረግ ብቃት አላቸው። ቅዠት ይሰጡልሃል ከዛ በተለየ ምንም አያደርጉልህም። አንተ ግን ለሷ “ጥሩ ወንድ” ለመሆን የማይገባትን መስዋትነት ትከፍላለህ። ወጪ እና ወዝህ ለሷ የሚገበር ይሆናል። ለአንድ ቀዳዳ ብለህ 99 ቀዳዳዋን ትደፍንላታለህ።
የዚህ አለም አንቀሳቃሾች የሚያደርጉትን ያውቃሉ ስለዚህም ነው በየሚዲያው የተገላለጠች ሴትን የሚያቀርቡልን። ህይወታችንን ሁሉ የዝሙት ባሪያ እንድንሆን የታሰበ እውነተኛ ወንድነትን የሚገድል አደንዛዥ ዕፅ ነው።
ነገር ግን እመነኝ ይህ ጥሩ ሰው መልካም ወንድ ለመሆን የምትጋጋጠው ሁሉ በመጨረሻ ያበቃል። በጭንቀት ተወጥረህ በሰዎች ተረስተ እራስህን ታገኘዋለህ። በአንተ ትከሻ ላይ አልቅሳ። ስልክ ቁጥሯ ከማያውቀው ሌላ ወንድ ጋር ሄዳ ትተኛለች። አንተ በሷ ፍቅር አሸን ግጥም ጽፈህላት። እሷ ግን ስሟን በቅጡ ሳያውቅ በተሳሳተ ስም ለሚጠራት ወንድ መፅሃፍ የሚያህል ቴክስቶች ትጽፋለች። አንተ ፍቅርህን መግለጫ ብዙ ዘፈኖች ትጋብዛታለህ። እሷ በአንድ ወንድ ምክንያት ዘፈን ከፍታ ታለቅሳለች። አንተ ለእሷ ወንድ አይደለህም አንተ ለእሷ የስሜት ማገዶ ነህ። ዝም ብሎ ማሟሟቂያ ማደመቂያ..
እውነተኛ ወንዶች ለፍቅር አይለምኑም። ፍቅር ደም አፋሳሽ አይደለም ይልቅ የሚገነባ የደስታ ገንቦ ነው። እየሄድክ ነው፣ እየራቅክ ነው፣ እያሸነፍክ ነው። በድንገት ከብዙ ጊዜ በኋላ ወደኋላ ዞር ስትል ብዙ ሴቶች ተከምረው ትመለከታለህ። ስለዚህ አጫዋች ጆከር የምትሆንበትን የጨዋታ ዝርዝር አቃጥለው!። አስቂኝና አልጋጭ ቪድዮዎችን አስወግድ። ልክ እንደሮም ሜዳ በመድረኩ ያሉት እንደሚሳለቁብህ እና እንደሚዝናኑብህ አትሁን። በእግር የሚረገጠውን ኳስ እስከመሳም፤ ጊታሩም ስሜትህን እስሚነካ አትጠብቅ። አዕምሮህን እጠብና ቀና በል።
ሴትን ማክበር ለሴት ፍላጎት መንበርከክ አይደለም። ሴትን ማክበር ለራስ መትረፍ ነው። እራስን ግዛና ለራስህ መልካም የሆነውን ሁሉ አድርግ። በማንም የማትታለል፣ ማንም የማይቆጣጠርህ በማንም የማትተካ ሰው ሁን።
እ ቅ ድ
ኃ ይ ል
ሆኖ መገኘት!
አንተን የሚገነቡህ ተራ የጠዋት ፅሁፎች እና ስሜታዊ አስለቃሽ ታሪኮች አይደሉም። የእሷን አላማ ለማሳካት እዚህ አልተገኘህም።
“አንቺ የእኔ ጨረቃ ነሽ” አትበል፤ ጨረቃ ሰማይ ላይ ነች። ጨረቃ ፍጹም የማትነቃነቅ፣ ሰዓቷን የምታከብር፣ በጨለማ ግዜ የማትረሳ እጅግም የምታበራ ነች። ስለዚህም ተራውን ከግዙፉ አትመጥን። ፈጽሞ እንደጨረቃ አትሆንልህም!። ይሄ በህይወት ሳለው የተማርኩት ትምህርቴ ነው። እና ይህ ሁሉ ከንቱ ነገርህ ይበቃል
ወንድ ሁን…!
ብልህ ሁን..!
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza
