10 Apr 2026, Fri

ሶስቱ ሊቆጠቡ የሚገባቸው ነገሮች { ክፍል ሁለት }

ስኬታማ ህይወት ለመኖር መቆጠብ ስለሚገቡን ነገሮች በጀመርነው ሃሳብ መሰረት ባለፈው ፖስት ስለ ጊዜ ቁጠባ አስፈላጊነት ተመልክተናል፡፡

ዛሬ የምንመለከተው ስሜትን ስለመቆጠብ ነው፡፡

ብዙ ሰዎች ስሜት የሚቆጠብ አይመስላቸውም፡፡

በቀን ውስጥ የሚገጥሙን ነገሮችና ያለን የስሜት አቅም ካልተመጣጠነ ስሜት እየባከነ ነው ማለት ነው ፤ የዚህ ምልክቱ የውስጥ ዝለት ፣ ነገን ለመጋፈጥ አለመፈለግ ፣ ድብርትና የመሳሰሉት ስሜቶች ናቸው፡፡

ስሜትን ለመቆጠብ . . .

፩. መተው የሚገባንን ነገር መለየትና መተው፡፡
አንዳንድ ሰዎችና ሁኔታዎች ትተናቸው ዘወር ካላልን በስተቀር በመጨረሻ ስሜትን ከማዛልና ከማድክም ውጪ ፋይዳ የላቸውም።

በጭቅጭቅ ፣ በእልህና በመሳሰሉት ሁኔታዎች እንድንቆይ ከሚያደርጉን ሰዎችና ሁኔታዎች ዘወር ማለት ስሜትን ይቆጥባል፡፡

፪. አሉታዊ ሃሳቦችን አለማሰላሰል፡፡

ሁል ጊዜ ያልተሳኩልንንና የሚያስፈሩንን ማሰላሰል ይህ ነው የማይባል ስሜትን የማባከን አቅም አለው፡፡

አሉታዊ ሃሳቦች እንዳይመጡብን ማድረግ ባንችልም  እነሱን ከማሰላሰል ቀነስ በማድረግና በአዎንታዊው መቀየር ስሜታችንን እንዳያሟጥጡት መከላከል እንችላለን፡፡

፫. ስሜትን ማስተንፈስ፡፡

በየእለቱ የሚገጥሙንን የስሜት ውጥረቶች ለማረጋጋት በየእለቱ መንፈሳዊ ልምምድን ማዳበርና ጸሎት ማድረግ ፣ ከተለመደው የአካባቢ ኡደት ዘወር በማለት ፈታ ማለት ፣ ለቅርብና የልባችን ለሆነ ሰው የስሜታችንን ሁኔታ ማካፈል ይገኙበታል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች በመለማመድ ስሜታችሁን ስትቆጥቡ ይህ ልምምድ ከሌላቸው ሰዎች የላቀ ነገርን ማከናወን ትጀምራላችሁ፡፡

ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *