ከዕለታት አንድ ቀን፣ አንድ ስኬታማና ሀብታም ነጋዴ ወደ አንድ መንደር ጎራ ይላል፡፡ በመንደሩ መሀል ሲያልፍም አንድ ወጣት በከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ሆኖ መንገድ ዳር ተቀምጦ ያገኘዋል፡፡
ነጋዴውም ቀረብ ብሎ “ልጄ ሆይ! ምን ሆነህ ነው እንዲህ የምታዝነው?” ሲል ይጠይቀዋል። ወጣቱም ”ጌታዬ! በዚህ ዓለም ላይ ዕድል የለኝም፤ ምንም ብሰራ አይሳካልኝም፤ ድህነትና ውድቀት ብቻ ነው ዕጣ ፈንታዬ” በማለት መረረ፡፡
ነጋዴውም ፈገግ ብሎ “እንግዲያውስ እኔ መፍትሄ አለኝ፤ ግን ለምሰጥህ እርዳታ አንተም የምትሰጠኝ ነገር ይኖራል” አለው፡፡ ወጣቱም በደስታ “ምንም ይሁን ምን እሰጥዎታለሁ” አለ፡፡
ነጋዴው ፦ “ሁለቱን ዓይኖችህን ስጠኝና እኔ 1 ሚሊዮን ብር እሰጥሃለሁ” አለው፡፡
ወጣቱ ደነገጠና “እንዴት ሆኖ? ዓይኖቼን ከሰጠሁማ ማየት አልችልም፤ በምንም ተአምር አልሰጥህም!” አለ።
ነጋዴውም ፦ “እንግዲያውስ ሁለቱን እጆችህን ስጠኝና 500 ሺህ ብርልስጥህ” አለው፡፡
ወጣቱም “በፍጹም! እጆቼ ከሌሉ እንዴት እሰራለሁ? አልስማማም!” አለው፡፡
በመጨረሻም ነጋዴው እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ! ተመልከት፤ አንተ እኮ ገና ሳትጀምረው ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ውድ ሀብቶች (ዓይን፣ እጅ፣ ጤና) አሉህ፡፡ ፈጣሪ በሚሊዮን የሚቆጠር ካፒታል በነፃ ሰጥቶህ ሳለ ‘ዕድል የለኝም’ ብለህ ማልቀስህ ስህተት ነው፡፡ ትልቁ ስኬት ያለው እጅህ ላይ ባለው ሀብት ተጠቅመህ ለመስራት ስትነሳ ብቻ ነው።
ወጣቱም በነጋዴው ንግግር ተደንቆ፣ ማማረሩን ትቶ ባለው አቅም ለመስራት ቆርጦ ተነሳ፡፡
ከታሪኩ ምን ትምህርት እንውሰድ?:-
ብዙዎቻችን የሌለንን ነገር በማሰብ እናማርራለን፤ ነገር ግን ያለንን ትልቅ የጤና እና የጉልበት ሀብት ዘንግተነዋል፡፡
ትልቁ የዕድል መክፈቻ ቁልፍ እጃችን ላይ ያለው ጤና እና ለመስራት የምናደርገው ጥረት ነው፡፡
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza
