የሰው ልጅ ዓይኑ የተሰራው “የጎደለውን” ብቻ እንዲያይ ሆኖ ነው እንዴ ? ሙሉ ጤና ይዘን “ጫማዬ አላምር አለ” ብለን እናማርራለን።
የሚበላ አተን ሣይሆን “የፈለግኩት ምግብ አልቀረበም” ብለን እንናደዳለን።
እስኪ ለአፍታ ቆም ብለን “ሀብታችንን” እንቁጠር።
፩. የጤና ዋጋ (The Price of Health)
ሆስፒታል ገብተህ ታውቃለህ?
ኦክስጅን ለመተንፈስ ስንት እንደሚከፈል ታውቃለህ?
አንተ ግን በነጻ እየተነፈስክ፣ “ኑሮ ከበደኝ” ትላለህ።
ኩላሊት እጥበት ክፍል ገብተህ አይተህ ታውቃለህ?
አንተ ግን ሽንትህን በነጻ እየሸናህ፣ ምስጋና የለህም።
ባለፀጋ ማለት አካውንቱ የሞላ ሳይሆን፣ ጤናው የተሞላ ሰው ነው።
አልጋ ላይ ሆኖ ሚሊዮን ብር ከሚቆጥር ሰው፣ እግሩ ላይ ቆሞ ሻይ ከሚጠጣ ድሃ፣ ማነው ባለፀጋ?
ወዳጄ… በጤና መኖርህ ራሱ “ትልቅ ትርፍ” ነው።
፪. የሌላው ሰው ህልም
አንተ የምትጠላው ስራ፣ የስንት ስራ አጦች ህልም እንደሆነ ታውቃለህ?
አንተ የምታማርርበት ቤት፣ የስንት ጎዳና ተዳዳሪዎች ህልም እንደሆነ ታውቃለህ?
አንተ የምትጨቃጨቅባት ሚስት/ባል፣ የስንት ብቸኞች ምኞት እንደሆነች ታውቃለህ?
እኛ ያለንን ነገር የምናውቀው፣ ያጣነው ቀን ነው። እስካለን ድረስ “መብት” ይመስለናል። ሲወሰድብን ግን “ጸጋ” እንደነበር ይገባናል።
ያለህን ነገር ውደደው፤ ካልሆነ ግን የሚወደው ሰው ይወስድብሀል!
፫. የንጽጽር ወጥመድ
ደስታችንን የሚሰርቀው ሌባ ማነው? ንጽጽር
(Comparison)!
“ጓደኛዬ መኪና ገዛ፣ እኔ ግን በእግር ነኝ።”
“ጎረቤቴ ፎቅ ሰራ፣ እኔ ግን ኪራይ ነኝ።”
ህይወትህን ከሌላ ሰው ጋር እያወዳደርክ፣ ያንተን በረከት አታርክሰው። የእሱ ሰዓት (Time zone) እና ያንተ ሰዓት ይለያያል። እሱ በ25 አመቱ ያገኘውን ፣ አንተ በ40 ልታገኘው ትችላለህ።
ወይም እሱ ያገኘውን ገንዘብ፣ አንተ በጤናና በሰላም ተክተህ አግኝተህ ይሆናል።
አምላክ ለሁሉም የሰጠው የራሱ የሆነ “ጥቅል” (Package) አለው። የሰውን ጥቅል እያየህ ከመቅናት፣ ያንተን ጥቅል ፍታና ተጠቀምበት።
የጭሰኛው መልእክት…
ከእንቅልፍህ ስትነሳ… ስልክህን ከመነካካትህ በፊት፣ ደረትህን ንካ።
ልብህ ይመታል? ትተነፍሳለህ?
Congratulations እንኳን ደስ አለህ! ዛሬም በህይወት አለህ። ይሄ ትልቅ እድል ነው።
ዛሬን ለማየት ያልታደሉ ስንት አሉ?
ስለዚህ…
• ስላለህ ነገር አመስግን።
• ስለጎደለህ ነገር ስራ።
• ስለሌላው ነገር አትጨነቅ።
ምስጋና የደስታ ቁልፍ ነው። ቁልፉ እጅህ ላይ እያለ፣ በሩ ተዘጋብኝ ብለህ አታልቅስ!
ጭሱ ከኔ ፣ እሳቱ ከአንተ !
ይህ እውነት የአንተንም የሌላውንም ህሊና ከነካ፣ ዝም ብለህ አትለፈው።
ራሳችንን እንፈትሽ ፡ ራሳችንን እንመልከት።
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
t.me/danelroza
ለፌስቡክ
Fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
linkedin.com/in/danelroz
