ቼ ጉቬራ (Ernesto “Che” Guevara) በ1928 በአርጀንቲና ተወለደ። በሕክምና ሙያ ምሩቅ ቢሆንም ዓለም የሚያውቀው ግን በአብዮተኛነቱ ነው። በላቲን አሜሪካ የሚያየው መገለልና ፖለቲካዊ ግፍ እውነታን በቀጥታ እንዲያይ አደረገው። ይህ ልምድ እርሱን ከሕክምና ወደ አብዮታዊ ፖለቲካ አመራው፣ ግፍን መቃወም የሕይወቱ ዋና ዓላማ እንዲሆን ጋበዘው።
በ1950ኛዎቹ መጨረሻ ቼ ጉቬራ ከፊደል ካስትሮ ጋር በመተባበር በኩባ አብዮት ውስጥ ታላቅ ሚና ተጫወተ። አብዮቱ ከተሳካ በኋላ በመንግሥት ውስጥ ኃላፊነት ቢወስድም፣ ለእርሱ ዝም ብሎ ሥልጣን መያዝ ብቻ በቂ አልነበረም። ግፍ በሌሎች አገሮች እየቀጠለ እያለ መቆየት ከኅሊናው ጋር አልተስማማም፣ ስለዚህ አብዮቱን ወደ ሌሎች አገሮች ለማስፋት ተጓዘ። የግፉዓን የነፃነት አርማ የነበረው ቼ በ1967 በቦሊቪያ እየተዋጋ ሳለ ተይዞ ተገደለ።
ዳሩ ግን እርሱ ቢሞት ሐሳቡ አልሞተም፤ “ዝም ብሎ መኖር ከግፍ ጋር መተባበር ነው” የሚለው አመለካከቱ እስከዛሬ ድረስ ብዙዎችን ያነቃቃል። ቼ ጉቬራ በታሪክ ውስጥ ግፍን የሚቃወም የነፃነት ምልክት ተደርጐ ይቆጠራል።
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza
