“አማካኝ ተሰጥኦ ፣ አማካኝ ምኞት እና አማካኝ የትምህርት ደረጃ ያለው ሰው ግራና ቀኝ የማይልና ያተኮረ ግብን ይዞ ከተከተለ በሕብረተሰቡ መካከለ ከሚገኝ አለ የተባለ አስደናቂና ሊቅ ከሆነ ሰው አልፎና ልቆ ሊገኝ ይችላል” – Mary Kay Ash
እስቲ ዛሬዋን ቀን አንድ ቁም ነገር ለራሳችሁ እንድትሰሩ ልሞግታችሁ፡፡
ብዙ ሰዎች በህይወታቸው ካለ ምንም ግብ ነው የሚኖሩት። ከእነዚህ ካለምንም ግብ ከሚኖሩት ብዙ ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ደግሞ ግብን የማያወጡበት ምክንያት ግብን እንዲያወጡ የሚያደርግ የራዕይ አቅጣጫ ስለሌላቸው ነው፡፡
ስለሆነም ብዙ የእውቀት ፣ የገንዘብ ፣ የልምድ እና የወዳጅ (Connection) ባለጠግነት እያላቸው እንኳን በየቀኑ ፊታቸው የመጣላቸውንና ያገኙትን እያደረጉ ፡ አንድም ነገር ሳይገነቡ ጊዜያቸውን ያባክናሉ፡፡
ህይወታችሁ አቅጣጫ እና ጣእም ያለው እንዲሁን ከፈለጋችሁ ፦
፩. ራዕያችሁ ምን እንደሆነ ለይታችሁ እወቁ፡፡
ራዕያችሁን ለማወቅ ባላችሁ ጉዞ ትልቁ እንቅፋት የራእይን ትክክለኛ ትርጉም ያለማወቅ መሆኑን አትዘንጉ፡፡
፪. ባወቃችሁት ራዕያችሁ መሰረት ግቦችን አውጡ፡፡
ግቦቻችሁ የአንድ ዓመት ፣ የአምስት ዓመትና የአስር ዓመት የጊዜ ሁኔታዎችን ያካተቱ መሆናቸውን እርግጠኛ ሁኑ፡፡
፫. ባወጣችኋቸው ግቦች መሰረት የየእለት ተግባራዊ እርምጃን ጀምሩ፡፡
ግብ ማለት ነገ የሚደረስበት ዕቅድ ሲሆን የተግባር እርምጃ ደግሞ ወደ ግቡ የሚወስድ የየዕለት እንቅስቃሴ መሆኑን እወቁ፡፡
ራዕይ የሌለው ግብ የማውጣት ሙከራ ግራ ያጋባችኋል፡፡
ተግባራዊ እርምጃ የሌለውም ግብ ደግሞ ከምኞት አያልፍም፡፡
ከራዕያችሁ አንጻር ግብ አውጡ ! ከግቡ አንጻር ደግሞ ስራ ጀምሩ ! አንዴ ከጀመራችሁ ደግሞ አታቁሙ !
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza
