የመፅሀፍ ርእስ : መመለስ
ደራሲ : ብርቱካን ሚደቅሳ
አሳታሚ : ር-ኖቦት አታሚዎች
የህተመት አመት: ታህሳስ 2018
የገፅ ብዛት: 292
መግቢያ ፤
የተወለዱት በአዲስ አበባ ፈረንሳይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የመጀመርያ ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በህግ ሁለተኛ ድግሪያቸውን ከሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በህዝብ አስተዳዳር ወስደዋል የአንዲት ሴት ልጅ እናት የሆኑት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ዳኛ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንትም ነበሩ በዳኝነትም ይሁን በፖለቲካው መስክ ትልቅ ስም ያላቸው ወ/ሪት ብርቱካን በኢትዮጲያ ህግ የበላይነት እንዲከበር በከፈሉት መስዋአትነት እና በጥንካሬአቸው በአርአያነት ሲጠቀሱ በያዝነው ወርም መመለስ የሚል ርእስ የሰጡትን መጽሀፍ በታላቅ ድምቀት አስመርቀው ለገበያ አቅርበዋል ‹‹ስራ ከጀመርኩበት ከ 1989 ጀምሮ የአደባባይ ሰው እንደመሆኔ መጠን የህይወት ታሪኬን የመፃፍ ጉዳይ በጉትጎታም በምክርም አስታኮ የመጣብኝ ጊዜያት በርካታ ናቸው ›› ገፅ 1 የሚሉት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በመፅሀፍ ልፃፍ አልፃፍ በእውኑ ለመፅሀፍ የሚሆን ታሪክ አለኝ ወይ ምን ተሰራና ይፃፋል በሚል ሀሳብ ይቸገሩ የነበሩ ሲሆን በዚህ መሀልም መፀሀፍ ለመፃፍ ያልተሳኩ ሙከራዎችን አሳልፈዋል ፡፡
የከሸፈ ሙከራ ፤
መፅሀፍ ለመጻፍ ቢያመነቱም በሌሎች አማካኝነት መፅሀፍ ሊፃፍ መንገድ ተጀምሮ የከሸፈባቸውን መንገዶችን አስፍረዋል መጀመርያ በስደት በሄዱበት እና ሁለተኛ ድግሪያቸውን በተማሩበት ወቅት በተለይ እዛ ያለ አሜሪካዊ ፕሮፌሰር እና ባለደረቦቻቸው ያካፈላቻቸውን የህይወት ታሪኳን መሰረት በማድረግ ወደ ዶክመንተሪ ከዛም ወደ መፅሀፍ እንዲመለስ ቢጠይቋትም አልፈቀደችም ለዚህም መልሷ ‹‹ በኢትዮጲያ የፖለቲካ ሰፈር ያደረኩት ሁሉ አገለግል ብየ አገልግየም በኢትዮጵያም የህዝብ አስተዳደር ለገዥ ሳይሆን ለዜጋ ያደላ ነገረ ስርአት አመጣ ያቅሜን አዋጣለሁ ብየ የወደድኩትን ህልሜን ወደ እውነታ ለማስጠጋት መጣሬ አልቀረ…ሆነው ግን ፍፁም ሌላ ታዲያ ይሄ ህይወት ምኑ ይፃፍለታል የስቃይ እና የመከራ ታሪክ ቀርፆ እዩኝ ማለት ፅፎስ አንብቡኝ ይባላል ›› ገፅ 2-3 በማለት የፊልም ቀረፃ እና የመፅሀፍ ስራ እንደማይሆን አሰረዳኋቸው ይላሉ ሁለተኛው ያልተሳካ ሙከራ በ 2008 የፒበዲ አዋርድ አሸናፊ አሜሪካዊ ታሪኳን በበይነ መረብ ካነበበ በኋላ በታሪኳ በመሳብ ታሪክሽ የለየለት የመትረፍ እና ወደ ጥንካሬ የመመለስ ነው በማለት በመፅሀፍ ታሪኳን ለማዘጋጀት ቢከጅልም ፈቃደኛ መሆን አልቻለችም ከነዚህ ያልተሳኩ ሙከራዎች በኋላ ወደ ሀገር ተመልሰው ምርጫ ቦርድን መርተው ሲሰናበቱ በተለይ ከባልደረቦቻቸው የቀረባለቸው ታሪክሽ በመፅሀፍ አስፍሪ ጥያቄ ተቀብለው ይህን መፅሀፍ ‹‹ ብዙ ፍቅር ለሰጠኝ እና ብርሀን ለሰጠኝ ማህበረሰብ (ቤቴ) ለበጎነት የፅሁፍ ሀውልት ላቆም ብድሯን ስለመመለስ ነች መልሼ የማልችለው ቢሆንም ›› ገጽ 12 በማለት መፅሀፍ ለመፃፍ መብቃታቸውን ይገልጻሉ ብርቱካን ሚደቅሳ በመፅሀፉ በተለይ ያሳለፈቸውን የፖለቲካ ጉዞ የበለጠ በመጽሀፉ ታሰፍረዋለች ተብሎ ቢጠበቅም በመፅሀፉ የራሷን ትውስታዎች የሰፈሯን እና ብሎም የሀገሯን ታሪክ አሰባስባ ስለአብዮቱ፤ ስለ ፍትህ ፤ስለ ፍቅር፤ ስለ ሰብአዊነት እና ማህበራዊ ታሪካችን ሀዘንና ደስታችንን በሰዋዊ ቋንቋ የተረከችበትን መመለስ ስትል ርእስ የሠጠችውን መፀሀፍ አበርክታለች ፡፡
የእንቢዎች ሰንሰለት ፤
ለወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በተለይ ወደ ፖለቲካው መግባት እንደ እርሾ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የቤተሰቧ አባል የሆነው የአጎቷ ዘውገ ገ/መድህን መንገድ ይመስላል የኢህአፓ አባል የነበረው እና ከኢህአፓ ጋር ይታገል የነበረው አቶ ዘውገ ገ/መድህን ከቀይ ሽብር በፊት ህይወቱ ያለፈው ሲሆን የአቶ ዘውገን ታሪክ ከቅርብ ቤተሰቧችዋ የተነገራትን እንዲህ ታስቀምጠዋለች ‹‹ ሀዘኔ ጨርሶ እናቴ ያልተዋጠላት ስለነበርለእኔ የህልሜ አለም ሰው ስለሆንም በህይወት ካሉት አጎቶቼ በበለጠ እያወራችኝ ነው ያደኩት ››ገጽ 51 በማለት እንዴት በአጎቷ እንደተሳበች ትገልጻለች ፡፡ከዚህ በተጨማሪም አጎቴ የሞተለት ኢህአፓ ይሉትን ድርጅት ምኑንም ከማወቄ በፊት ገና ልጅ እያለሁ ነው ይህን ስሜት በውሰጤ ያገኘሁት ‹‹ በቃ የአጎት ታሪክ ተደግሞ ተደግሞ ለቆመለት ዓላማ መስዋአትነትን መክፈል መፍቀዱ አጥብቆ ሳበኝ ›› ገፅ 52 የምትለው ብርቱካን ሚደቅሳ በአቶ ዘውገ መንገድ ተጉዛ እድሜም እውቀትም ጨምሬ ዘውገ ህይወቱን ካጣ ከ 28 አመት በኋላ እኔም እንደ ዘውገ ለአቅመ መሰዋአትነት ደረስኩ ታሰርኩ ቤት ለማስበርበር ልክ እንደ እንደ ዘውገ በፖሊስ ተንጠልጥየ መጣሁ ››ገፅ 52 በማለት በተለይ በእስር ወቅት ያሳለፉትን የተለያዩ ችግሮች እንደያልፉት የለ እንደሚባለው ነው ሲሉ ባመኑበት መንገድ መጓዝን እንቢ የማለትን መንገድ ከኢህአፓው ጭዳ ዘውገ ገ/እግዚያብሄር መከቷሏን ትገልፃለች ፡፡
የብርቱካን ዳናዎች ፤
የህይወት ታሪኳን ደጉሶ በያዘው መፅሀፍ ከማለዳ የህይወት ጅማሬ አንስቶ በህይወት ሀዲድዋ ውስጥ የምትመላለሰው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ‹‹የኔ የኔታ›› በሚል ርእስ ከልጅነት ሀሁ፤አቡጊዳ፤መልእክተ ወንጌል፤ካዛ ዳዊት ከደገመችበት የልጅነት ጊዜ በመነሳት ቀጥሎ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርቷን ስለተማረችበት የሚያዚያ 23 ት/ቤት ስለነበሯት የትምህርት ቤት እና የመምህራኖች ገጠመኞች በሚገርም ትውስታ አስቃኝታናለች ከዚህ ባለፈ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ላይ በተለይ ስድስተኛ እና ስምንተኛ ክፍል የነበራት ከፍተኛ ውጤት በልዩነት አብረዋት ከተማሩ የፈረንሳይ ለጋሲዮን ተማሪዎች በልዩነት በመነን ት/ቤት ከፍተኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች የሚማሩበት / Special Class/ እንድትመደብ እንደደረጋት በተለይ ከፈረንሳይ መነን እሩቅ ነው በማለት ያላት ከፍተኛ ውጤት ለመነን የልዩ ክፍል ውስጥ እንዳስገባት እዛ የነበረችበት የ 4 አመታት የትምህርት ጊዜ ወደ ኋላ መለስ ብላ ለማሳየት ሞክራለች በሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ለማምጣት የነበራት ትጋት በተለይ ስለ ማትሪክ ፈተና እንዲሁም በሂሳብ ብቻ/ MATHIMATICS /“C” በማምጣቷ ሳቢያ ወደ ህግ ት/ቤት መግባትዋን አውግታናለች ከዚህ ጎን ለጎን በአስራዎች አፍላ እድሜ ስለነበሩ የፍቅር ጥያቄዎች የአቻ ጓደኛ ግፊት ያንን ተቋቁሞ አላማን ከግብ ማድረስን እንዲሁም የዳኝነት ህይወቷን የፖለቲካ ጅማሬዋን በ1992 በግል ለፓርላማ መወዳደሯን እንዲሁም ከ 1997 ምርጫ ጀምሮ የሄደችበትን የፖለቲካ መንገድ ለማሳየት ሞክራለች ከዚህ ባለፈ ሌሎች የሄደችባቸውን የህይወት መስመሮች በነቂስ ለማሳየት በመፅሀፉ ተመላልሳለች ፡፡
ፈረንሳይ ለጋሲዮንን በመስታወት ፤
ትውልዷ በፈረንሳይ ለጋሲዮን የሆነው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በዚህ መፅሀፍ ከፖለቲካው ይልቅ ማህበራዊ ህይወቷን በተለይ የኢትዮጲዊያን ማህበራዊ ህይወትምን እንደሚመስል በፈረንሳይ ለጋሲዮን በኩል ለማሳየት ሞከራለች ከዚህም አንዱ በፈረንሳይ ስለሚገኙ እና በተለይ የሰፈሩ ታላላቅ አባቶች ስለሚያዘወትሩበት የሰፈሩ ጠጅ ቤቶች፤ስለ ቀድሞ ሰፈሮችና በፈረንሳይ ለጋሲዮን ስለሚገኙ ታሪካዊ ስፍራዎች፤የፈረንሳይ ነዋሪ ስለሆኑት የቀድሞ ታዋቂ አትሌት ዋሚ ቢራቱ ብዙም ያልተነገረ የቅድስና ተግባር ስለ ሰፈሩ ማህበራዊ መስተጋብር በፈረንሳይ ስለሚከበሩ የንግስ በአላት በተለይ የግንቦት ልደታ ከቅድመ ዝግጅት እስከ ማጠናቀቂያው ጢንቀት በተሰኘው ርእስ ስር በተለይ የሀይማኖት እና የአደባባይ በአል የሆነው ጥምቀት በአል አከባበር በፈረንይ ለጋሲዮን ምን እንደሚሚስል አሳይታናለች የለም ባዳ በተሰኝ ንኡስ ርእስ ስር የቀረበውና በተለይ በ1990ዎቹ የሀገሪቱ ራስ ምታ ስለነበረው እና ብዙ ወጣቶች ስለቀጠፈው የኤድስ በሽታ በተለይ በቤታቸው ተከራይታ ትኖር ስለነበረው ወለላ የተባለች እንስት ታሪክ ዋቢ በማድረግ ወለላን ለማዳን ለማሳከም ማድረግ የሚገባቸውን ከቅርብ ጎረቤት ጋር በመሆን ያደረጉት ስዋዊ ተግባር ዳሩ የወለላን ህይወት ባያተርፍም ህይወቷ ካለፈ በኋላም ወለላ እድር ባይኖራትም የፈረንሳይ ለጋሲዮን ነዋሪዎች የለም ባዳ ብለው ማንም እድር ላለው ሰው የሚደረገውን አድርገው ግብአተ መሬት መፈፀሙን ከትባልናለች በዚህ እንደ ሀገር ይዘነው የመጣነውን ልንለቅ የማይገባንን ሰብአዊ ተግባር ለማሳየት ያስቻላት ሲሆን አንባቢም በተለይ ቀድሞ ያለችውን የፈረንሳይ ለጋሲዮን ሰፈር በምናብ ልክ እንደመስታወት ገልፃ አሳይታናለች ፡፡
ያልፖተለኩ ፖለቲከኞች ፤
በምርጫ ዘመን ዋዜማ በተለይ በሀገሪቱ የሚታተሙ ታዋቂ ጋዜጦች ሪፖርተርን ጨምሮ በሚዘግቡት የፓርላማ ክርክር (በተለይ በአቶ በድሩ አደም እና ሌሎች በወቅቱ የነበሩ ጉምቱ ፖለቲከኞች) በሚያደርጉት ክርክሮች ሳቢያ በግል ለመወዳደር እንዲሳቡ እንዳደረጋቸውና እና በማግስቱም የምርጫ ህግጋትን ወደ ማንበብ መግባታቸውን ሲገልፁ የመወዳደር ሀሳባቸውን ለወደጆች ቢያከፍሏቸውም በከፊል ድጋፍ ሲያገኙ በከፊል ነቃፌታንም አስተናግደዋል ቢሆንም በምርጫ 1992 የወረዳ 12/13 የግል ተወዳዳሪ በመሆን እና የምርጫ ምልክታቸውን ጭራ በማድረግ ተመዝግበው ተወዳድረዋል ፡፡በዚህ የመጀመርያ በሆነ የፖለቲካ ጉዟቸው በተለይ ከአንድ ጋዜጠኛ ተብየ የሚደርስባቸው ማስፈራርያ በተለይ ስም የማጥፋት ዘመቻ ሙከራ በጋዜጦች ላይ ስምሽን አጠፋለሁ በየጋዜጣው ስምሽን ከማጥፋቴ በፊት መኝታ ተጋሪኝ የሚል ከፍተኛ የፆታዊ ጥቃት ሙከራ እንደረሰባቸው አስፍረዋል ያልፖተለኩ ፖሊከኞች እንደምትለን ብርቱካን በወቅቱ በፖለቲካው የማይሳተፈው ደበበ ደፌራ የተባለ ወዳጃቸው ደፋር ጋዜጠኛ ተብየወን አደብ እንዲያሲዝላት ማድረግ ስትችል ከዚህ ባለፈ ለምርጫ ቅስቀሳ የግል ተወደዳሪ እንደመሆኗ መጠን የቅስቀሳ ዘዴዋ የመወዳደርያ ፖስተር በየአደባባዩ መለጠፍ ሲሆን በዚህ የካሰች ገ/ማርያም እገዛ የበረታ ነበር የሚሉት ወ/ሮ ብርቱካን የምርጫው ዘመንም በኢህአዴግ ወፈ ሰማይ ካድሬ ግጥሚያ በእኔ መሸነፍ ተጠናቀቀ በማለት የሚገልፁት የሚሉት ወ/ሪት ብርቱካን ፖለቲከኛ ሳይሆኑ እሳቸው ለተሳተፉበት የፖለቲካ ተግባር የተባበሯቸውን ወዳጆች ያልፖተለኩ ፖለቲከኞች በማለት ተግባራቸውን በመፅሀፉ አካተውላቸዋል፡፡
ብርቱካን የኢህአዴግ ፍሬ ፤
ለቅንጅት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርነት ተመርጣ ሁለ ነገር ተካሮ ወህኒ በገባችበት እና ከማእከላዊ እስር ቤት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት በምትንገላታበት ወቅት በተለየዩ ሚዲያች በተለይ በአይጋ ፎረም የገዢው ፓርቲ ደጋፊ የሆኑ ሰዎች ‹‹ ብርቱካን የኢህአዴግ ፍሬ ናት ›› እየተባለ ይፃፍ ነበር የሚሉት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ‹‹ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት ደግሞ በአጭሩ ብርቱካን ኢህአዴግ ባመጣው ስርአት ተጠቅማ ዳኛ ሆነች፤ምርጫ የተወዳደረች ብሎም የፓርቲ መሪ የሆነቸው ፍሬያችን ናት ›› ገፅ 245 ይህን መስማት ለእኔ ግርምት ነው የፈጠረብኝ የሚሉት ወ/ሪት ብርቱካን ‹‹ ያለ ሀጤአቴ ቀፍድደውኝ ሲያበቁ ፍሬአችን እያሉ ራሳቸውን ሲያሞግሱ ያፈራነውን የምንቀረጥፍ ነን ብለው እየተኩራሩም እንደሆነ እንዴት አይገባቸውም ›› ገፅ 245 በማለት የነበረውን ተቃርኖ ይገልፃሉ ፡፡
በተለይ የጉርምስና እድሜዋን በዘመነ ደርግ የእርስ በእርስ ጦርነት በርትቶ አብዝታ የምትሰማው ራድዮ ቀኑን ሙሉ ‹‹ ግፋ በለው› ሲል የበአሉ ግርማ ኦሮማይ ስርጭት ተክልክሎ በፎቶ ኮፒ ብቻ ስታነብ በድብቅ ቪ.ኦ.ኤ ታዳምጥ የነበረችው ብርቱካን ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በተለይ በሚደረጉ የምርጫ ክርክሮች በኢህአዴግ የፖሊሲ ሀሳቦች መማረኳን የማትሸሽገው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከ1992 ምርጫ ላይ ለኢህአዴግ የነበራት አዎንታዊ አመለካከት ሙሉ ለሙሉ አልተሸረሸረም ፡፡‹‹በፍርድ ቤት ቆይታየ የመጀመርያ አመታት ራሱ በውሀ ቀጠነ ሰዎች እስር ቤት ሲታጎሩ እና ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሲቀፈደዱ ሳይ ዋነኞች አለቆች ሳያውቁት ሊሆን ይችላል ወይም አልገባቸው ይሆናል በሚል አእምሮየ ስንቴ ምህረት ሊያደርግላቸው ሞክሯል ›› ገፅ 252 በማለት ለኢህአዴግ የነበራቸው አዎንታዊ አመለካከት ለአመታት ያልከሰመ የነበረ ቢሆንም በስተመጨረሻ የሆነው ሆኖ እድሜ ለስየ አብርሀ ጉዳይ የኢህአዴግ እይታየ ላይጠገን ተሰበረ በማለት ወደ ሰላማዊ ትግል እንድትገባ ሌላ መነሾ እንደሆናት ትገልፃለች ፡፡
ፈረንሳዊው ጎረቤቴ ፤
የፈረንሳይ ለጋሲዮን ፍሬ የሆኑት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በመፅሀፋቸው ከሳፈሩት ሌላኛው እውነት በተለይ በወቅቱ የአትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሰደር ከነበሩት ስቴፋን ጎምፕርትዝ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ነው ጥቅምት 1998 ቅንጅቶች ተጠራርገን ቃሊቲ ከመግባታችን በፊት ከአንድ ሁለት ቀን በላይ አላገኘሁትም ቃሊቲ ከወረድን በኋለ ሌሎች አምባሳደሮች እንደሚያርጉት እሱም እየመጣ ይጎበኛቸው እንደነበር እርቅም እንዲመጣ በመመላለስ ወትውቶናል የሚሉት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ይህ የፈረንሳይ አምባሳደር ወ/ሪት ብርቱካን ቃሊቲ እስር ቤት ድረስ ዘልቆ ጠይቋል ለዚህም ምክንያቴ ጎረቤቴ ነሽ የሚል ነው ከዚህ ባለፈ የብርቱካን ቤተሰቦችንም ቤት ድረስ በመምጣት ይጠይቅ እንደነበር አልሸሸጉም ዳግም ከመጀመርያ እስር ከተፈቱ በኃላ ታህሳስ 20 ቀን 2001 አ.ም ወደ ቃሊቲ የወረዱት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በወቅቱ የስራ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ ሀገራቸው ሊያቀኑ የነበሩትን አምባሳደር የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒሰቴር መለስ ዜናዊ ያላቸውን መቀራረብ ተገን በማድረግ የብርቱካን ጉዳይ አወያይተዋል የውይይቱም ፍሬ ሀሳብ ‹‹ ይቅርታ ሳልጠይቅ ቀርቼ እስር ቤት ብገባ ድጋሚ የመውጣት እድል እጀግ ዘለግ ያለ ዘመንን እንደሚወሰድ የፈለጉትን ይቅርታ መንግስታቸውን ካልጠየኩ በዚህኛው ዙር እስር አድሜ ልክ የፀና እንደሚሆን እና ምናልባት 25 አመታት የእርጅና ዘመን ሰደርስ የእስር ቤት አስተዳደር ካመነበት በአመክሮ ሊለቀኝ የሚችል መሆኑ ነው›› ገፅ 256 የሚል ሲሆን ከዚህ በኋላ ነው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አንገት አስደፊ ያሉትን ይቅርታ ጠይቀው የእድሜ ልክ የተባለው እስር ቀርቶ ከ 18 ወር እስር በኋላ ነፃ መውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን ለዚህም ጎረቤታቸው የነበሩት የአምባሳደሩ ሚና ከፍተኛ ነበር ፡፡
አልፀፀትም ፤
ከአፍላ ወጣትነት ጀምሮ በግል ተወዳደሪነት ለፓርለማ እስከ መወዳደር ብሎም የተቃዋሚ ፓርቲ ከሌሎች ጓደኞች ጋር ፓርቲ መስርቶ እስከመታገል ካዛም ባለፈ ከአንድም ሁለት ጊዜ ረዘም ላሉ ጊዜያት በእስር መማቀቅ ብሎም በመንግስት ግልበጣ እና ሙከራ ተጠርጥራ ሞት እስኪፈርዳባት ተጠየቅ የቀረበባት እና ሌሎች ክስተቶች ያሳለፈቸው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በእስር ጊዜ ፍርድ ቤት በምትቅርበብት ወቅት የነበረውን የወላጅ እኗቷን ሁኔታም አልዘነጋችም ‹‹ በመሀል ወደ ቤተሰብ መቀመጫ ሰፍራ ሳይ እናቴ ፊቷ በላብ ተዘፍቆ መነሳት አቅቷት ወንበር ላይ ተቀምጣ ቀርታለች በምልክት ምንም አይሆንም አይዞን ለማለት ሞከርኩ አታየኝም ሰማይ ምድሩ ዞሮባትል ›› በማለት ከሷ ባለፈ የእናቷን ስቃይ አካፍላናለች ፡፡በመፅሀፏ ፈረንሳይ ለጋሲዮን የማኅበራዊ ህይወት እንዳሳየችን ሁሉ በተለይ በእስር በነበረችበት ወቅት የሰፈሯ እጅጉን መረበሸን አልሸሸገችም ፡፡
‹እኔ ከታሰርኩበት ጥቅምት 22 1998 ጀምሮ ለበርካታ ሳምንታት ፈረንሳይ ሰፈራችን የከረመቸው የጦርነት አውድማ መስላ ነው መጀመርያ ይህን ያየሁት ከማእካላዊ እስር ቤት ለብርበራ በሚል ጥቅምት 25 ወደ ቤቴ ይዘውኝ ነው የሰፈሩ የሰፈሩ የውስጥ ለውስጥ መንገድ በአድማ በታኝ ትጥቅ በታጠቁ በርካታ የፌደራል ፖሊስ ተወሯል ከመኖርያ ሌላ አንዳች ነገር የሌለበት መንደር ውስጥ ገብቶ ከሰው ደጃፍ ላይ ገፋ ሲልም ቤቱ ውስጥ ጦርነት የሚገጥም ፖሊስ ፈጣሪ ያሳያችሁ›› ገፅ 263 በማለት የነበረው ሁኔታ ትገልጻለች በሷ እስር ወቅት እንደዛ የታመሰ ሰፈር በተቃራኒው በሷ ከእስር መፈታትን ተከትሎ ፌሸታ ሲሆን የቀየው ወጣቶችም የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጅተው ለብርተካን መኪና ሸልመዋል አዎ በዚህ መፅሀፍ የተጠቀሱና እና ያልተጠቀሱ በተለይ በወህኒ ቤት ያሳለፈቸውን ከባድ ጊዜያት በሄድኩበት መንገድ ፈፅሞ አልፀጸትም የዋዛ ላልሆነው የነፃነት መንገድ እንኳንም ህይወቴን ሰጠሁ ብየ አምናለሁ ምክንያቱም ከኢትዮጲያና ከህዝቦቿ የማይፈዝ ደማቅ ፍቀር ይዞኛልና ይላሉ ፡፡
እንደ መውጫ ፤
በተለይ በ1997 ምርጫን ተከትሎ ብቅ ካሉ ደፋር ፖለቲከኞች መካከል አንዷ የሆነችው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የህይወት መስመሮቿን ያሳየችበትን መፅኀፍ ማበርከቷ ለሌሎችም አርአያ መሆን የሚችሉት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ መመለስ በተሰኘ መፅሀፋቸው ውለታውን ቆጥሬ ለማልጨርሰው በደስታም በሀዘኔም ከጎኔ ለነበሩ የሰነ ፅሁፍ ሀውልት ይሆን ዘንድ ውለታ ለመመለስ የቆመ ሀውልት ነው የሚሉት ወ/ሪት ብርቱካ ሚደቅሳ መፅሀፍ በሽፋኑ አይገመትም እንዲሉ በዋናነት ውስብስብ የሆነውና ያለፉትን የፖለቲካ ጉዞ በስፋት ያሰፍራሉ ተብሎ ቢጠበቅም ለየት ባለ መል ከልጅነት እስከ እውቀት ያለውን የሕወታቸውን ክፍል ገልፀው ማስነበብ ችለዋል ይህ መፅሀፍ በተለይ ወ/ሪት ብርቱካን ከ 1997 ምርጫ በኋላ ለሚያውቃቸው ለሀገሩቱ ህዝብ የበለጠ እርሳቸውን ያውቅ ዘንድ እድል የሰጠ ነው በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ያልተካተቱ እርሳቸው ዘንድ ያሉ ሌሎች ፖለቲካዊ ወጎችን ይዘው በቀጣይ መፅሀፍ ይመጡ ዘንድ እየጠየኩ በዚህ ላብቃ ፡፡
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza
