በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚታዩ ውጫዊ ገጽታዎች ስለ አጠቃላዩ የጤና ደህንነት ብዙ እንደሚናገሩ ጥናቶች ያሳያሉ። በውጫዊው የሰውነት ክፍል ላይ የሚታይ ምልክትም ውስጣዊ የጤና ችግር ስለመኖሩም ማሳያ ነው።እነዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምልክቶች ደግሞ አንዳች የጤና እክልን ማሳያዎች ናቸው።
■ አይን ፦የአይን የታችኛው ቆዳ ላይ የሚታይ የመሸብሸብ እና የማበጥ ምልክት ሲኖር፥ ጨው የበዛበት ምግብ አብዝተው በመውሰድ ጤናዎን አደጋ ላይ እየጣሉ መሆኑን ያሳያል።
ከዚህ ባለፈም ከፍተኛ መጠን ያለው የአልኮል መጠጥ እየጠጡ ከኩላሊት ጋር የተያያዙ የጤና እክሎችን እያስተናገዱ ነው። ምናልባትም ሲወስዷቸው ለእርስዎ ሰውነት የማይስማሙ የምግብ አይነቶች እንዳሉም ማሳያ ነው፤ ወተትና የወተት ተዋጽኦ ወይም ደግሞ የስንዴ ዘሮች።የአይንዎ ቀለም ወደ ቢጫነት ከተቀየረ ደግሞ የጉበት በሽታ ተጠቂመሆንዎን ያመላክታል::
■ ቆዳ ፦የእርጅና ምልክት ተደርጎ የሚታሰበው የቆዳ መሸብሸብ ከአጥንት ጋር የተያያዙ ከፍተኛ ችግሮች መከሰታቸውን ማሳያም ነው።አየሩ ቀዝቀዝ ሲል ደረቅ፣ የቀለም መቀየር እና የሚያሳክክ ምልክት በቆዳ ላይ ሲከሰት ደግሞ፤ ከመተንፈሻ አካል ጋር የተያያዘ የጤና እክል እንዳለ የሚያመላክት ነው።የቆዳ ላይ ሽፍታ እና ቀይ ነጠብጣብ ምልክቶች ደግሞ፤ ከፍተኛ ጭንቀት፣ ድብርት እና ፍርሃት ሲበዛ የሚከሰቱ ናቸው።
■ ፀጉር ፦በጊዜ ሂደት የሚፈጠር የፀጉር መሳሳትም፥ ከጭንቀት፣ ከተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ አልፎ አልፎም በእርግዝና ወቅት፣ በሚወሰድ የወሊድ መከላከያ መድሃኒት፣ የክብደት መቀነስ እና መጠነኛ የጤና እክል መኖሩን ማሳያ ነው።
■ ከንፈር ፦ደረቅ እና የተሰነጣጠቀ ከንፈር ሰውነት ከፍተኛ የሆነ የፈሳሽ መጠን እንዳነሰው ማሳያ ነው።ሰውነት የሚያስፈልገው ቅባት ሲያንሰው እና ይህን ተከትሎም መገጣጠሚያ አካባቢ ችግር መፈጠሩንም ያመላክታል።የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም መዳከሙንና በባክቴሪያ ወይም በሌላ ተዛማጅ ቫይረስ ከንፈር ላይ ጉዳት መድረሱን ማሳያም ነው።
■ ጥፍር ፦ጥፍር ሲሰነጠቅ እና ሲሰረጎድ ሰውነት ውስጥ ያለ የብረትመጠን ማነስ፣ የደም ማነስ እና ከልብ ጋር የተያያዘ ችግር እንዳለ ማሳያ ይሆናል።ጥፍር አብዝቶ ነጭ ሲሆን ወይም ሃምራዊ የሚመስል ቀለም ሲይዝ ደግሞ የጉበት እና ኩላሊት ላይ አደጋ ስለመኖሩ ማሳያ ነው።
እናም እነዚህ ምልክቶች ሲከሰቱ ችላ ከማለት የህክምና ባለሙያ ማማከር እና ተገቢውን ክትትል ማድረጉ አስፈላጊ ነው።
ሰላም እና ጤና ከእናተ ጋር ይሁን
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza
