10 Apr 2026, Fri

በአእምሮ እውቀት ማደግ ማለት ከፈጣሪ የተሰጠንን አእምሮ በማሻሻል ለስኬታማ ሕይወት የሚበጀኝን ነገር ማዳበር ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች እውቀታቸውን ሳያሳድጉ የኑሮአቸው ደረጃ ግን እንዲያድግ ይፈልጋሉ፡፡

በእውቀት የማደጋችንና የኑሮአችን ጥራት ደረጃ ግን ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አላቸው፡፡ አንድ ሰው ወደ ተግባራዊነት ሊለውጠው የሚችለውን እውቀት በመቅሰምና በዚያም በማደግ ልቆ ሲገኝ ከዚያው ጋር የኑሮው ደረጃ እየላቀ መሄዱ ጥርጥር የለውም፡፡

የእውቀታችን መጠንና የኑሮአችን ደረጃ ሊፋታ የማይችል ትስስር አላቸውና፡፡

በዚህ ሳምንት የሚከተሉትን እርምጃዎች ውሰድ፡-

1. የተከፈተልህን ለይ
በቀላሉ የሚበራልህንና አእምሮህ የተከፈተለትን የእውቀት አይነት ለይተህ ማወቅ አለብህ፡፡ ይህም ማለት መሆንና ማድረግ ከምትፈልገው ነገርና ለማወቅ ከምትጓጓለት የእውቀት አይነት አንጻር ራስህን ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡

2. አንብብ
መጽሐፍ የማንበብ ልማድህ እንዴት ነው? በሳምንት ውስጥ ስንት ምእራፍ ታነባለህ? ጀምረህ የጨረስካቸው መጽሐፍቶች ምን ያህል ናቸው? እነዚህን ጥያቄዎች በቁም ነገር ጠይቅና ራስህን በማየት ለውጥን አድርግ፡፡

3. የተግባር ሰው ሁን
አንብበህ የቀሰምካቸውን እውቀቶች በተግባር ካላዋልካቸው ከመረጃነት አያልፉም፡፡ ይህንን አስታውስ፣ መረጃ እውቀት አይደለም፡፡ ያዳበርካቸውን እውቀቶች ወደ ተግባር ማዋል ወይም ያንን ለማድረግ በማቀድ ላይ መሆን አለብህ፡፡

ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *