አዲሱ ደራሲ

ወደ ወጣት ደራሲያን ከማምራታቸው በፊት እጂግ አጠር ባለ መልኩ የደራሲ ሚናው ምንድነው ብለን እንመልከት።
አንባቢውን ማነቃቃት ወይም ( to inspire)
አንባቢውን እውቀቱ እንዲፈትሽ ማረግ (to challenge )
አንባቢውን ማመላከት ወይም መምራት ( to give guidance)
እንዲሁም እውቀት ማካፈልና ማዝናናት እና የመሳሰሉት ይገኙበታል።
አዲሱ ትውልድ ወይም ለውጥንና ብልጽግናን የሚሻ ትውልድ ምን አይነት እራእይ ሊኖረው ይገባል?
፩ ፡ ማንኛውም ሰው በተለይ ደግሞ አንድ ጸሃፊ ማየት የሚፈልገውን ለውጥ ሆኖ መገኘት አለበት።
ስለ ሰላም መጻፍ የሚሻ ሰው ወይም ሰላም ለአንባቢዎቹ ለማበርከት የሚሻ ደራሲ። መጀመሪያ የውስጡን ሰላም ፈልጎ ማግኘትና እራሱን ለሰላም ዝቅ ያረገ መሆን ይገባዋል።
የምንሻው ለውጥ አገራችን በአንባያን እና ንግግራቸው ሰማሁ እያሉ አሉባልታን ማስተጋባት ሳይሆን፤ አነበብኩ እዚህ ሃሳብ ላይ ምን አይነት አመለላይ እና ምን አይነት አስተያየት አላችሁ የሚል ዜጋን ለመፍጠር፤ መጀመሪያ እኛ አንባቢ መሆን ይገባናል። እንደ ፍኖት፣ ሎሬት፣ አለምጸሃይ እና ሃዲስ የመሳሰሉት በሰሜን አሜሪካ እና ካናዳ የሚገኙ የጥበብ መድረኮች እንዲሁም በአገር ውስጥና አውሮፖ የሚገኙ መድረኮች እንዲበረክቱ እንዲጠናከሩ ከፍተኛውን ድርሻ መውሰድ ይጠበቅብናል።
እንደ ፀሃይ ሳሎን አይነቱ የመጽሃ ክለብ ወይም ደግሞ የመፀሀፍ ትንተና የሚደረግበት ክለቦች ሰፍት እንዲቋቋሙ የተቋቋሙት እንዲበረቱ ድጋፉችንን መስጠት ያስፈልገናል።
አንድ እራእይ ያለው ደራሲ የሚፈልገውን ለውጥ ሆኖ መገኘት ግድ ይላል።
፪ ፡ አንድ ደራሲ አዳዲስ ዕይታወችን የመቅረጽና ሃሳቦችን የማፍለቅ አስተዋጾ ሊኖር ይገባል። በርግጥ ባህልን እና ስርአትን ማክበር አግባብ የሚሆንበት ቦታ ቢኖሩም፤ ሁሉንም ነገር ይሄ የኛ ባህል አይደለም ብሎ ከመተው፣ ተመሳሳይ ችግሮችን ሌላው አለም እንዴት ተወጣው ብሎ መመልከት ከዛም የወሰድትን ጠቃሚ ሃሳብ ከራስ ትውልድ ጋር ማጋባት ያስፈልጋል።
አማኬሊ የተባለች የሩዋንዳ ጸሀፊ (ሌፍት ቱ ቴል) እንድናገር ተረፍኩ፤ የተሰኘው መጸሀፍዋ ላይ እጂግ የሚገርምና የሚዘገንን የሩዋንዳን እልቂት አስፍራለች። ታዲያ እጂግ በፈጠነ መልክ ወደዚያ እልቂት እያመራች ያለች አገር ከነሱ ስህት ምን ልትማር ትችላለች? ከዚያ ሁሉ እልቂትስ በሗላ ሩዋንዳ ተመልሳ እንዴት አገር ሆነች? ከዚያስ ምን እንማራለን ። ይሄንንስ እጂግ ጠቃሚ ሃሳብ ሃሀር ውስጥ ላሉ ለአንባቢያን እነሱን እነሱን በሚል ወይም አገር አገር በሚሸት ቋንቋ እንዴት ማስተላለፍ እችላለሁ? የሚለውን እይታ ማዳበር ያስፈልጋል።
፫ ፡ እውነተኛነት
የዛሬ መቶ አመት የተፃፈ እውነት የተሞላ መጸሀፍ አሁንም እውን ነው። ከመቶ አመት በሗላም እውነት ነው ከዚያ በሗላም እንደዛው። አሜሪካኖች (you can never be honest and boring at the same time) የሚል አባባል አላቸው።
ቲክ ና ሀ የተባሉ ጠቢብ ዘ አርት ኦፍ ኮምንኬሽን የተሰኘው መጸሃፋቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል። አንድ ወቅት ላይ ህንድ አገር ስሄድ ከባድ የእርስ በርስ ጦርነት ላይ ደረስኩ። ከዚያ የነበሩ ጋዜጠኞች አንተ ዛሬ ጋዜጠኛ ብትሆን ኖሮ ምን ታረግ ነበር ብለው ጠየቁኝ። ጥቂት ከአሰብኩበት በሗላ እንዲህ ብየ መለስኩላቸው።
እውነቱን ተናገሩ። ለዚህም ለዚያ በማያደላ መልኩ። እዚህኛውም እዛኛውም ውስጥ የፍራቻን፤ የጥላቻን እና የበቀልን ዘር በማይዘራና ሌላ እልቂትን በማያስከትለው መልኩ ዘግቡ አልኳቸው።
እሱን ማድረግ ይቻል ይሆን ላለኝ ጋዜጤኛ መልሴ ከመጻፍህ በፊት አንድ ሰው ሌላውን ለምን በጭካኔ ሊያጠፋው ይነሳል የሚለውን ጥያቄ ጠይቅና መልሱን ለማግኘት ሟችንም ገዳይንም እኩል በርብር አልኩት ይሌሉ።
አንድ ደራሲ የአስተሳሰብ ለውጥን ለመፍጠር በእውን የተመረኮዘና አድሎአዊ ያልሆኑ መነጋገሪያ፣ ስራዎችን ለአንባቢዎቹ በማበርከተ ብስለትን መቅረጽ ይችላል።
፬ ፡ ሁሉም ሰው መጸሀፍ ነው።
አንድ ወቅት ላይ አንድ ወዳጄ የአንባሳደር ዘውዴን ማረፍ አስታኮ እጃችን ላይ ያሉት ታላላቅ ወርቆች፣ ሀያል መጸሃፎች ደግመን የማናጌጥባቸው ወይም ደግመን የማንገልጣቸው መጸሀፎች እየሆኑ ነው እባካችሁ አጠገባችሁ ያሉትን ሰወች አናግሩዋቸው። ታሪካችሁን እወቁ እጃችንን ላይ ያሉት ወረቀቶችም ፎቶዎችም ተቀብላችሁ ኮፖ አርጎ የሚል ነገር ለጠፈ።
ይሄን ሃሳብ ይዤ ወደተወሰኑ ወጣቶች እና የእድሜ ባለጸጋ አመራሁ። ወጣቱ በከፊል ጥሩ ሀሳብ ነው ቢለኝም የበዛው ግን ከፈለገ እራሱ ይጻፍ እኛን አይጨቅጭቀን የሚል አስተያየት ሰጠኝ።
የእድሜ ባለ ጸጋዎቹም በከፊል የፈለግሽውን እንንገርሽ ቢሉኝም፤ እንኳን እናንተ ልትጠይቁ ይቅርና እንንገራችሁ ስንላችሁም ታፌዙብናላችሁ የሚል ቅሬታቸውን አሰሙ።
ታሪኩን የማያቅ ስህተቱን ይደግማል ይባላልና። እራሳችንን ከዚያ ለማዳን፤ ለመማር ወይም እውቀትን ቆመው ከሚሄድት መጸሀፎቻችን ከመሰብሰብ አንቆጠብ። ከዚያሲያፍ ደግሞ ለማስተማር ወይም የአወቅነውን ለማሳወቅ። ለሌላው ተንቀሳቃሽ መፀሀፎች የመሆን ግዴታወችንም ወርሰናል።
አያት ቅድማቶቻችን ቲሪክ በምሳሌ፣ ተረት ተረት፤ አለቃ ገብረሃና እያሉ መጻፍና ማሳተም
ባልቻሉበት ዘመን ይቆያል ወጎችን የምንቀጥልበት ድምጽ መሆን አለብን።
፭ ፡ የምንጽፋቸው ጽህፈቶችም ሆኑ ሌሎች ስራዎቻችን ከኛ የተሻለ ዜጋ ለመፍጠር የተዘጋጁ መሆን ይገባቸውል። የተሻለ ጸሀፊ የተሻለ አንባቢ የተሻለ የአስተሳሰብ ብስለት ያለው። ካነበባቸው ወይም ካየው ተነሱቶ እሱን ለሚተካው ዜጋ የተሻለ ነገርን ለማፍለቅ የተዘጋጀ ለመሆን እንዲችሉ ማነጽ እና የትውልድ የደራ መውሰድ ከወጣቱ ፀሃፊ ይጠበቃል።
ባለፈው ሳምንት ስለገጠመኝ ነገር ላውጋችሁ።
ገብረ ክርስቶስ ደስታ እጂግ ከምወዳቸው እና ከማደንቃቸው ገጣሚወች አንድ ነው። አንዳንዶቹን ግጥሞቹን በቃሌ አነበንባቸዋለሁ። ታዲያ ባለፈው ሳምን አንድ ወዳጄ ጋር ቁጭ ብዬ አንድ ግጥም ትዝ አለኝና ከመሃሉ አንድ ሁለት ስንኝ አወረድኩ። አብራኝ የነበረች ውብ ወጣት አንድ ሁለት አከለችበት። በጣም ተደስቼ ገብረክርስቶስ ደስታን ታውቂያለሽ በጣም ደስ ይላል ብዬ አጨበጨብኩ። ትክ ብላ አይታኝ። እሱ ደግሞ ማነው እኔ የማውቀው የሚኬሌን ዘፈን ነው አለች።
ብደነግጥም አላዘንኩባትም ምናልባት ያለፉትን ውብ ስራወች ማንበር፤ እና ለነሱ ጥሩ ድምጽ መስጠቱና የማስተዋወቁን በነሱ ላይ ተመርኩዞ የተሻለ መፍጠርን አላዳበርነውም የሚል ሀሳብ መጣልኝ እንጂ።
የአወቁትን ለማሳወቅ ምን ላስተምር ወይም ምን ላካፍል ለሚለው ሃሳብ የምርምርና፣ የትምህርት መጸሃፎችን የሚጽፉ ቢኖሩም፤ እንደ በውቀቱ ስዬም እያሳሳቀ ቁምነገር የሚያጎርስ ጸሃፊ። እንደ ፍቅረማርቆስ ደስታ የህዝብን አኖዋኑዋርና ፍቅር በረቀቀ መልክ የሚገልጽ አስተማሪወችንም ሳንዘነጋ በቀልድና በመመሰጥ ውስጥ ለውጥን ማምጣትም የኛው ድርሻ ነው።
በመጨረሻም ማን እንደሆነ የተናገረው ባላውቅም አነድ ፀሃፊ ነፃነት የምትለዋን ቃል መጠቀም የጀመርክ ቀን ሃላፊነቱንም አብረህ ተረክበሃል ይላል። የተሰጠንን ነጻነት ተጠቅመን የምንጽፋቸው ነገሮች በሙሉ መጸሃፍ፣ አርቲክል፣ ኦን ላይን ሃላፊነት የታከለበት እንዲሆን እጅግ አርጌ አደራ እላለሁ።