10 Apr 2026, Fri

፩. ተስፋ አድራጊ መሆን ረጅም ርቀት ይዞህ ይሄዳል፡፡

በጣም አስከፊ በሆኑ ጊዜያት እንኳ ተስፋ ባለመቁረጥ ችግሮችን መጋፈጥና ለመቀየር መቁረጥ የመፍትሄ መላ እንዲመጣልን ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ተስፋ አትቁረጥ፣ ጨለምተኛ አትሁን፡፡ከፈተና ባሻገር የሚገኘውን ድል አስብ።

፪. መርህ ፣ አቋም ፣ ያመንክበት ጉዳይ ይኑርህ ነገር ግን ለመስተካከል ቦታ ይኑርህ፡፡

በደረስክበት እውቀት መሰረት በነገሮች ላይ አቋም ሊኖርህ ይገባል፡፡ ነገር ግን የህይወት ዘመን ሁሉ ተማሪ ከሆንክ በአንድ ወቅት የያዝከው አቋም ትክክል እንዳልሆነ ስትረዳ ያመንክበትን ጉዳይ ማስተካከል ይኖርብሃል፡፡

፫. አዋዋልህን እና ጓደኞችህን ምረጥ፡፡

አስተሳሰብህን እና ድርጊትህን በገንቢ ጎን ከሚተቹና ከሚገነቡ ሰዎች ጋር የምታደርግ ከሆነ በየጊዜው እየተሻሻልክ የምትሄድ ሰው ትሆናለህ፡፡ ባህሪህ እና ህይወትህ እያደር የሚመስለው የጓደኞችህን ነው፡፡

፬. መሆን የምትፈልገውንና መስራት የምትፈልገውን በጊዜ አውቀህ ጀምር፡፡

በወጣትነት ጀምረህ መርጠህ የምትሄበት መንገድ እያደር አንተንም እየቀረፀህ ስለሚሄድ በዛው የመቀጠል እድል ይጨምርልሃል፣ አይቻልም ለሚሉህ በቀላሉ ላትሸነፍ ትችላለህ፣ በእድሜህ ብዙ ሳትገፋ ስኬታማ እና ብዙ ተፅእኖ አምጪ ትሆናለህ፡፡ የራስህን ራእይ የማትገነባ ከሆነ ሌሎች ቀጥረውህ ራእያቸውን እንድትገነባላቸው ያደርጉሃል፡፡

፭. ከሌሎች ጎበዞች ጋር በጥምረት ስራ፡፡

ከጎበዞች ጋር በጥምረት ስትሰራ አንተ የማታውቃቸውን ነገሮች ያሳውቁሃል፣ አንተ ልታገኛቸው የማትችላቸውን ሰዎች እንድታገኝ እድል ይከፍቱልሃል፣ ይበልጥ ወደፊት ያራምዱሃል፡፡

፮. በቅፅበት ከፍተኛ ደረጃ እደርሳለሁ አትበል፡፡

ከትምህርት ቤት አንደወጣህ ወዲያው ሃብታም፣ ባለስልጣን፣ ወይም ስኬታማ እሆናለሁ ብለህ አትጠብቅ፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ቢኖርህ እንኳ ስኬታማ ለመሆን ብዙ ልምድ ያስፈልግሃል፡፡

፯. ስለ ስህተቶችህ ሌሎችን ሳይሆን ራስህን ውቀስ ተማርባቸው፡፡

ስህተቶች እንድንቆጭባቸው ሳይሆን እንድንማርባቸው ካደረግን ደግመን አንሰራቸውም፡፡

፰. ምርጡ ትምህርት ቤት ኮሌጅ ሳይሆን ህይወት ነው፡፡

ምንም ያህል መፅሀፎች ብታነብ፣ ፈተናዎችን ብትወስድና ብታልፍ፣ በህይወት ሂደት የምትማረውን ያህል ብቁ አያደርጉህም፡፡ ስራዎች እና የስራ ሃላፊዎች ያስተምሩሃል፣ ያበቁሃል፡፡

፱. ህይወት ሁሌም የቀና አይደለም፡፡

በህይወት ጉዞህ ትገጫለህ ትወድቃለህ፡፡ ኑሮ ፈተና ነው፣ ጌም መሳይ ነው፣ ተነስተህ እስኪሳካልህ ጉዞህን ቀጥል፡፡

፲. ለስኬታማነት ትእግስት እና ጠንክሮ መስራት ያስፈልግሃል፡፡ በአቋራጭ የሚመጣ ዘላቂ ስኬት የለም፡፡

፲፩. ለራስህ ክብር ይኑርህ ፣ በማንነትህ ኩራ፡፡

እያንዳንዳችን የተለያየን ስለሆንን ራስህን ከሌላው ጋር እያወዳደርክ ዝቅተኝነት አይሰማህ፡፡ በሌላው ውስጥ የሌለ አንተ ውስጥ ያለ ችሎታ ስላለ ፈልገህ አግኘው፣ ተቀበለው፣ እዛ ላይ አተኩር፣ አዳብረው፣ በራስህ ተማመን፡፡ ስኬታማ የምትሆነው በዚህ መንገድ ነው፡፡

፲፪. ራስህን አታሳብጥ፡፡

ስኬታማና ታላቅ የመሆን ራእይ መሰነቅ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ዛሬ ላይ ብትወጣ ነገ ደግሞ ታች መውረድ ሊገጥምህ ይችላል፡፡ ላይ መውጣትህ የብዙ ነገሮች ጥምር ውጤት ስለሆነ ራስህን አይነኬና ልዩ ፍጡር አድርገህ አታስብ፡፡

፲፫. “ደሃ ሆነህ ተወልደህ ከሆነ ጥፋቱ የአንተ አይደለም፤ደሃ ሆነህ ልትሞት ከሆነ ግን ጥፋቱ የአንተ ነው”።

ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *