10 Apr 2026, Fri

ፍሬድሪክ ዊልሃም ኒቼ ጀርመናዊ ፈላስፋ፤ ባህላዊነትን ተቺ እና የፊሎሎጂ ባለሙያ ነበር። ስራው በዘመናዊ ምሁራዊ ታሪክ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሳያሳድርና ወደ ፍልስፍናም ከመቀየሩ በፊት ክላሲካል ፊሎሎጂስት ሆኖ ስራውን ጀመረ። philologisቱን በባዝል ዩኒቨርስቲ በ1869 በ24 አመቱ የክላሲካል ሊቀመንበሩን በመምራት ላይ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በእድሜ ታናሽ ሰው ለመሆን በቃ።

ኒቼ በ1879 ዓ.ም በህይወቱ ባሰቃየው የጤና ችግር ምክንያት ስራውን ለቋል። በ1889 ዓ.ም በ45 አመቱ በቀጣዮቹ አስር አመታት ውስጥ አብዛኛውን ዋና ዋና ፅሁፉንም አጠናቋል። እና በ1897 ዓ.ም እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ከእህቱ ኤልሳቤት-ፎርስተር-ኒቼ ጋር በመሆን የቀሩትን ጊዜያት በእናቱ እንክብካቤ ውስጥ አሳልፏል። ከዚያም ግን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የአእምሮ ብቃቱን አጥቷል። የኒቼ ፅሁፍ ፍልስፍናዊ ቃላቶችን..ግጥሞችን..ባህላዊ ትችቶችን እና ልቦለዶችን ሲያጠቃልል በጥላቻ ውስጥ ያለን አስቂኝ ፍቅርንም ያሳያል።

እ.ኤ.አ. በ1889 ኒቼ በቱሪን ጎዳና የመጨረሻውን ቃል ተናግሮ ወደማይቀለበስ የእብደት ጉዞ ሄደ።

አንድ ሰውዬ በእጁ ጅራፍ ይዞ ፈረሱ ላይ እየጮኸ ደም እስኪፈሰው ድረስ ያለ ርህራሄ እየደበደበው ነበር። ኒቼም ወደ ፈረሱ ሮጦ አቀፈውና ስቃይ ባገነፈለው ስሜት ማልቀስ ጀመረ። ለሕይወት ጠንከር ያለ አመለካከት እንዳለው የሚታወቀው ይህ ፈላስፋ የፈረሱ አይን ምሕረትን ሲማፀን ሲመለከት በርኅራኄ ተሸነፈ። ኒቼ ፈረሱን አቅፎ እንባው በፊቱ ላይ እየፈሰሰ የሚያጽናና ቃል በጆሮው ሹክ አለው።

በቱሪን ውስጥ ኒቼ ከዚህ ምስኪን ፈረስ ጋር መገናኘቱ የርኅራኄ ጎርፍ አስከትሎበት ሙሉ በሙሉ የጥያቄ ሀዘን ዋጠው። የፈረሱ የተጨነቁ አይኖች የፈላስፋውን የነፍስ መስታወት የያዙ ይመስላሉ። ኒቼ ፈረሱን አቅፎ እንደያዘ ለጊዜው በተፈጠረው የስሜት ክብደት የተነሳ ልቡ ተሰበረ አእምሮው እንደታወከ ሊድን ወደማይችልበት የእብደት ጉዞ ውስጥ ገባ። በድንገትም ወደ መሬት ወድቆ እራሱን ሳተ ለሁለት ቀናት አልነቃም ነበር።

ከመውደቁ በፊት የተናገራት የመጨረሻም ቃሉም አንዲት ሐረግ ብቻ ነበረች ይባላል። የታሪክ አጥኚዎች ግን በሁለት መንገድ ያነሱታል የመጀመርያው “I understood” ሲሆን ሁለተኛው “I feel you” ነው። ከዛ በኋላ ቀሪ አመቱን ሙሉ በሙሉ ከአለም ተነጥሎ በእብደት ኖረ። እና እስኪሞት ድረስ አንድም ቃል አልተናገረም። ለደከመ እንስሳ ያለው ሰብዓዊ ርኅራኄው የመውደቁ ምክንያት ሆነ!።

የኒቼ አባባሎች ማለት ይከብደኛል። ምክንያቱም አባባሎችሁ ብዬ ባቀርብ ለአመታት የጻፍኩት አንድ መፅሐፍ ያህላል። ስለዚህ አንዱን ስተው አንዱ እየቆጨኝ የተመረጡትን ላቅርብላችሁ፦

«ትልቁን የደስታ ከፍታ የሚፈልግ ሰው እኩል የህመሙን መጠን ይቀበል..»

«አንድ ሰው አእምሮው ባዶ በሆነ ቁጥር የበለጠ ማኀበራዊ ይሆናል!»

«ሴት በጣም አስቀያሚ እና የማትስብ በሆነች ቁጥር ጩኸቷ እና ቅናቷ ይበልጥ እየጨመረ ይመጣል!።»

«ጭራቅ እንዳትሆኑ ከጭራቆች ጋር አትዋጉ ወደ ጥልቁን ብትመለከቱ ጥልቀቱ ደግሞ ወደ እናንተ ያያልና..»

«ከመጠን ያለፈ አስተሳሰብ ሰለባ እንዳትሆኑ፤ እውነትን መናገር ወደ ሰዎች እንደሚያቀርብ ማመን ከጀመርን የመቃብራችንን አፈር የመጀመርያ ቁፋሮ ጀምረናል። ሰዎች ከጥንት ጀምሮ የቀጧቸው፣ የገደሏቸው እውነት የሚናገሩትን ብቻ ነው። ከሰዎች ጋር ቆዩ እናም ውሸታችሁን አጋሩ። ምድራዊ ዘላለማዊነት ይሉታል ይሄ ነው።»

«ብልጥ ሰው ጆሮ ሳይነፍጉት ንግግሩን ያቆማል፤ ነገር ግን ንግግሩ ምንም ይሁን ምን አንድን ሰው ማናደድ ከፈለግን ስለ እሱ እውነተኛ ነገር ማውራት በቂ ነው!»

«አዳዲስ አብዮቶች ያስፈልጉናል። ቡድሃ ከሞተ በኋላ አሁንም በዋሻ ውስጥ ለዘመናት ግዙፍ አውልት ሰርተውለት አስፈሪ ጥላውን ሲከተሉ ኖረዋል። እግዚአብሔር ሞቷል ነገር ግን ሰዎች ባሉበት ሁኔታ አሁንም ጥላው ብቻ እያዩ ለሺህ ዓመታት ዋሻቸው ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ። እና እኛ አሁን ጥላውንም ማሸነፍ አለብን!።»

«ሴቶች..ከፍተኛውን ከፍ ያደርጋሉ ዝቅተኛውን ደግሞ ደጋግመው ዝቅ ያደርጉታል፤ ይህ የሴት ባህሪ ነው!።»

«እነዚህ ሰዎች አንዋሽም ብለው ይፎክራሉ፤ መዋሸት አለመቻል ግን እውነትን መውደድ ማለት አይደለም፤ ስለዚህም ተጠንቀቃቸው!»

«መንጋዎች ሁሌም እንደዚህ ናቸው፤ ሰውን የሚከተሉት ከፊታቸው ስለሚሮጥ እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም!።»

«ነገር ግን ልታገኘው የምትችለው በጣም መጥፎው ጠላትህ ሁል ጊዜ እራስህ ትሆናለ፤ በዋሻና በዱር ውስጥ ለራስህ ታደባለህ። ብቸኛው ሆይ ወደ ራስህ መንገድ እየሄድክ ነው፤ እና መንገድህ ከራስህ ልቆ ሰባቱን ሰይጣኖችህን አልፏል!። አንተ ለራስህ መናፍቅ እና ጠንቋይ፤ ሟርተኛ እና ሞኝ ተጠራጣሪ እና ያልደቀስህ ክፉ ሰው ትሆናለህ። እራስህን በራስህ ነበልባል ለማቃጠል ዝግጁ መሆን አለብህ.. አስቀድመ አመድ ካልሆንክህ እንዴት አዲስ ልትሆን ትችላለህን»

«እብደት እንደ ግለሰብ ብርቅ ነገር ነው፤ ነገር ግን በቡድን፣ በፓርቲ፣ በሕዝብ እና በዘመናት ውስጥ ደንብ ነው!።»

«ሰው ከእግዚአብሔር ስሕተቶች አንዱ ነውን? ወይስ እግዚአብሔር ከሰው ስህተቶች አንዱ?»

«እያንዳንዳችን በውስጣችን የሴት ምስል እንሸከማለን፤ ይህም ከእናታችን ምስል የተወሰደ ቅጂ ነው። ከዚህ በመነሳት ለሴቶች ያለን አመለካከት በእናታችን ይወሰናል፦ እናከብራቸዋለን፣ ወይ እንንቃቸዋለን አልያም ደግሞ ለእነሱ ግድ የሌለው ሰው እንሆናለን!።»

«እግዚአብሔር ሞቷል። እግዚአብሔር ሞቶም ይኖራል። እኛ ደግሞ ገድለነዋል። የገዳዮች ሁሉ ነፍሰ ገዳዮች ራሳችንን እንዴት እናጽናና?። ዓለም ከያዘችው ነገር ሁሉ እጅግ ቅዱሱንና ሃያል የሆነው እርሱ በኛ ቢላዋ ሥር ደሙ ፈሰሰ። ይህንን ደም ማን ያብሳል?፤ እኛነታችንን የሚያጸዳ የትኛውስ ውሃ ነው?፤ ምን ዓይነት የስርየት በዓላት፤ ምን ዓይነት ቅዱስ ጨዋታዎችን ልንፈጥር ይገባናል?። የዚህ ተግባር ታላቅነት ከእኛ በላይ ትልቅ አይደለምን?። እኛ ራሳችን አምላክ ለመሆን የተገባን ለመምሰል ብቻ እንደ አምላክን መሆን አይጠበቅብንም?።»

«በዚህ ገሃነም ውስጥ ታሞ ያልማቀቀ ሰው አለም ለእሱ ምስኪን ናት!።»

«ግን በመጨረሻም ፍቅር እውር ነው፤ ጓደኝነትም አይኑን ይጨፍናል!።»

«ሲደክመን..ከረጅም ጊዜ በፊት ባሸነፍነው አሳብ እንጠቃለን!።»

«በየትኛውም ቦታ አዲስ ገነት የገነባ ሁሉ በመጀመሪያ ኃይሉን ያገኘው በራሱ ሲዖል ውስጥ ነው..!»

«ስለዋሸሽኝ አላዝንም.. ከዚህ በኋላ ላምንሽ ባለመቻሌ ውስጥ አዝኛለሁ!»

«እውነተኛ ጓደኝነትን ሳይሰጡ ብቸኝነቴን የሚሰርቁኝን እጠላቸኋለው!»

«ህመም የሚሰማን እኛ በሆነውና ለራሳችን መሆን በምንፈልገው ፍጹም ምስል መካከል ያለውን ልዩነት ሁልጊዜ ስለምናይ ነው።»

«አሁን ግን ፍቅሬን ወደ እግዚአብሔር አዙሬያለሁ። እናም በእኔ እይታ ሰው ፍጽምና የጎደለው ፍጡር እንጂ ሌላ አይደለም፤ ብወደው ፍቅሩ ገደለኝ!።»

ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *