ላብ 99 በመቶ ከውሃ፣ ቀሪው አንድ በመቶ ከጨው፣ከፖታስየምና ከፕሮቲን ነው የሚሰራው፡፡ ዋና ተግባሩም ሰውነታን ከፍተኛ የሆነ ሙቀት ሲገጥመው አካላችንን ለማቀዝቀዝ የሚጠቀምበት ስልት ነው፡፡ ስለሆነም ላባችን የተፈጥሮ የሰውነት ሙቀት መቆጣጠሪያችን ነው ማለት ይቻላል፡፡ ቀጥለን ደግሞ አስደናቂ የላብ እውነታዎችን እናካፍላችሁ፡፡
- እያንዳንዳችን በመላ ሰውነታችን ከ2 እስከ 5 ሚሊዮን የሚደርሱ የላብ ዕጢዎች ይገኛሉ፡፡
- ሴቶች ከወንዶች በቁጥር የላቁ የላብ ዕጢዎች ቢኖራቸውም የወንዶች ዕጢዎች ግን ከሴቶች በእጥፍ ብዙ ላብ ያመነጫሉ፡፡ ይሁንና ሁለቱም ዕድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ የሚያመነጩት ላብ ይቀንሳል፡፡
- ምንም እንኳን ላብ ሽታ አልባ ቢሆንም ላብ ባላበን ወቅት በሰውነታችን ላይ የሚፈጠረው ሽታ የሚመጣው በቆዳችን ላይ በሚገኙ አንዳንድ ባክቴሪያዎች አማካኝነት ነው፡፡
- ከተለመደው የላብ መጠን በጣም ብዙ የሚያልባቸው ሰዎች ሃይፕርአይድሮሲስ የተባለ የጤና ችግር ሲያጋጥማቸው ሲሆን በመላው እንግሊዝ በዚህ ችግር ብቻ ከ2 ሚሊዮን ያላነሱ ሰዎች የዚህ ችግር ተጠቂዎች ናቸው፡፡
- ብዙ የላብ ዕጢ በብዛት ተከማችቶ የሚገኘው በእግራችን መዳፍ ሲሆን በአንፃሩ ጥቂት የላብ ዕጢዎች የሚገኙት በጀርባችን ላይ ነው፡፡ ብብታችንን ጨምሮ በክንዳችን ስር ብዙ ላብ የተፈጠረ እንዲመስለን የሚያደርገው ግን ቦታው ለንፋስ እምብዛም ያልተጋለጠ ስለሆነ በቀላሉ ላቡ ተኖ መድረቅ ስለማይችል ነው፡፡
- አንዳንድ ምግቦች የበለጠ እንዲያልበን ያድርጉናል፡፡ በቀጥታ ምግቦቹ ላብ የሚፈጥሩ ሳይሆን በሰውነታችን ውስጥ በሚቃጠሉበት ጊዜ ከፍተኛ ሙቀት ይፈጥራሉ፤በዚያን ጊዜ ሰውነታችን ሙቀቱን ለማቀዝቀዝ ላብ ያመነጫል፡፡ ለምሳሌ ቅመማቅመም የበዘባቸው ምግቦች እንደ ሚጥሚጣ፣በርበሬ፣ቃሪያ፣ሰናፍጭ፣ፌጦን የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
- የሰው ልጅ በየዓመቱ በአማካኝ 278 ጋሎን የሚገመት መጠን ያለው ላብ ያልበዋል፡፡
- በሰውነታችን ምንም አይነት የላብ ዕጢ የሌለባቸው ቦታዎች ጆሮአችን፣ከንፈርና ጥፍራችን ናቸው፡፡ ስለሆነም በእነዚህ አካባቢዎች ላብ ድርሽ አይሻልም፡፡
- እንደጣት አሻራችን ሁሉ የእያንዳንዳችን የሰውነት ጠረን ወይም ሽታ የተለየ ነው ማለትም ከማንም ጋር አይመሳሰልም፡፡
- ዘረመላችን የሚያልበንን መጠን ይወስናል፡፡ አንስተኛ፣መካከለኛና ከፍተኛ ላብ በሰውነታችን ውስጥ እንድናመነጭ ዋናው አዛዥ ዘረመላችን ነው፡፡
- ላብ ቀለም የለውም ነገር ግን በነጭ ቲሸርታችን ላይ ብዙ ጊዜ በብት አካባቢ ቢጫ ቀለም የሚታየው ላቡ ያመጣው ቀለም ሳይሆን ላቡ ከልብሳችን ጋር በሚፈጥረው ኬሚካላዊ መስተጋብር ነው፡፡
ጤናዎ የሁሉም ነገር መሰረት ነው!
የቴሌግራም ሊንክ ገብተው ሙሉ ጤና መረጃችንን መመለከት ይችላሉ።
ሰላም እና ጤና ከእናተ ጋር ይሁን
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza
