10 Apr 2026, Fri

ስለእኛ ፤

ስለ ዳንኤል ሮዛ

ዳንኤል ብሩህ አዕምሮና ልብን ያጣመረ በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከተፈጥሮ ፡ በፊት ከነበሩ ቀደምት አባቶቻችን እንዲሁም አሁን በዚህ ዘመን ካሉ መልካም የሆነውን ዕውቀት ለመማር እና ለመረዳት በጥልቅ የሚጓጓ ነው፡፡ ዳንኤል የሚለው ስሙ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን የስሙ ትርጉሙሙ ዳን እና ኤል ከተሰኙ ሁለት የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ሲሆን ዳን ማለት ፈራጅ ዳኛ ሲሆን ኤል የሚለው ቃል ትርጉም ደግሞ እውነተኛ አምላክ የሆነው የአምላክ ስም የሚወክል ሲሆን ኤል ማለት “ይሖዋ” የሚለውን የአንድ አምላክ ብቻ የሚጠራበት ስም የሚያመለክት (የሚወክል) ነው ፤ ሁለቱ የዕብራይስጥ ቃላት በአንድ ላይ ሲጠሩ ዳንኤል የሚል አንድ ትርጉም የሚሰጡን ሲሆን ትርጉሙም “ አምላክ ይፈርድልኛል ” “ አምላክ ፈራጄ ነው ” ማለት ይሆናል፡፡ ዳንኤል DANIEL የሚለውም ሣይሆን DANEL የሚለውን አጠራር ይጠቀማል፡፡

ዳንኤል በስነ-ጥበብ መስክ ሥራዎችን የሚሰራ ሲሆን ፡ በቴክኖሎጂው መስክን ኤል ቴክ በሚል ስያሜ በመሠረተው ድርጅቱ አማካኝነት የማህበረሰቡን ህይወት ለማቅለል የሚረዱ የተለያዩ ሥራዎችን የሚሠራም ነው፡፡ ዳንኤል የስነ-ጥበብ ሙያውን በመጠቀም የማህበረሰብ አስተሳሰብ ለውጥ ላይ የአተኮሩ የተለያዩ ሥራዎችን በስነ-ጽሑፍ ፡ በስነ-ራይም (በፊልም) በሬዲዮን እና በቴሌቭዥን ፣ በመድረክ ቴአትሮችን በአማርኛ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና በዓለም አቀፍ ቋንቋዎችን በመጠቀም ለማድረስ እየሰራ ይገኛል፡፡

ዳንኤል የጣዝማ ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነው፡፡ 

ስለዚህ የጦማር ገጽ ፤

በዚህ ብሎግ የዳንኤል ዕይታዎችን የማያቀርብበት ሲሆን ፤ ህይወታችንን በመልካም ጎዳና ለመምራት ጠቃሚ የሚሆኑ ጽሑፎችን ያጋራበታል፡፡ በአምላክ መኖር እና ከአምላክ ጋር ያለንን ዝምድና እንድናሳድግ ፤ ስለእውነት እና የሰው ልጆችን አጥምቆ ስለሚዘውረው የዚህ ዓለም “ እውነት ” የሚል ስያሚ ሰጥቶት ስለሚነዳን “በሀሰት ትርክት” እንድናውቅ የሚያሳዩን የተለያዩ ጽሑፎችን ያቀርብልናል፡፡

እኛ በምክንያት የምናምን ፤ አምላክ በሚጠቅመን ልክ የሰጠንን የመምረጥ ነጻነት በአግባቡ እንድንተቀም ፡ ይህን የመምረጥ ነጻነት በሌሎች አካላት እንዳይወሰደብን እና ሌሎች በነጻነት ሥም የእነሱን ምርጫ እንዳንኖር የሚያደርግ ፤ ከዚህ በፊት የተሰራብን ይህን መሰል አስተሳሰብ እንዴት ልንወጣ እንደምንችል መንገዱን የሚያሳዩ ሃሳቦችን የሚያሳዩን ጽሑፎችን የሚያቀር ሲሆን ፡ ይህም ከዚህ በፊት ስልምናደርጋቸው የእኔ ምርጫና ውሣኔዎች ናቸው ብለን የምናምንባቸውን ነገሮች ላይ “ ለምን ? ” ብለን እንድንጠይቅ መንገዱን የሚከፍትልን የሚያቀርባቸው የጽሑፎቹ ዋንኛ ዓላማዎች አንደኛው ነው፡፡

እስከዛሬ የምናምንባቸው ነገሮችን በሙሉ ቁጭ ብለን “ ለምን ? ”  በሚሉ ጥያቄዎች ራሳችንን መጠየቅ እንድንጀምርና ትክክለኛውን ምላሽ ከራሳችን ውስጥ እንድናገኝ ፤ ከአምላክ በስጦታ ያገኘነውን ውድ ህይወት በራሳችን ሙሉ ውሣኔ መወሰን እንድንችል ፤ በራሳችን ውሳኔዎችም ደስተኛ የህይወት መንገድን እንድንጓዝ እንዲሁም በራሳችን ውሣኔ እና ምርጫ ሌሎች በእኛ “ እውነተኛ ” ምርጫ ምክንያት ለምን የተለመደውን እና ሁሉም የሚከተለውን “ በሀሰተኛ ትርክት ” ላይ ተመስርቶ ከሚያደርገው ውሣኔ የተለየ በመሆኑ የሚያደርሱብንን ጫና እና ተጽዕኖ እንዴት እንደምንቋቋም የሚያስችሉንን ሃሳብ መንገዱን የሚያቀርብልን ይሆናል፡፡

በአምላክ ማመን የሚያስችሉን ተቆጥረው የማያልቁ ብዙ ምክንያቶችን ያሉን ሲሆን ይህን ዕምነት ከዚህ ዓለም የሀሰት ትርክት ጋር ለሚኖረን የዕለት ተዕለት ፍልሚያን ድል እንድናደርግ የሚያስችሉት ሃሳባቸው ፡ በጽሑፍ ፤ በቪዲዮ ፤ በድምጽ ብቻ በተዘጋጁ ፖድካስቶች ከወሬ በአለፈ ወደ ህይወታችን አውርደን ተግባራዊ ልናደርጋቸው የምንችላቸውን ሃሳቦችን የሚያቀርብበት መድረኩ ነው፡፡  

“ አምላክ ልጆቹ የሆኑትን የሰው ልጆችን በወደደበት ልክ ካልምን ተጨማሪ ምክንያት ከፊትም ሆነ ከሆላቸው ሳታስቀምጡ በንጹም ፍቅር ውደዱ ፤ ምንግዜም በክፉ ነገሮች አትሸነፉ ፡ ከዚህ ይልቅ ሁልግዜም ሰዎች ክፉ ነገሮችን ሲያደርጉባቹ ልክ እንደነሱ እንዳደረጉባቹ መልሳቹ ክፉ አታደርጉ ከዚህ ይልቅ የአደረጉባችሁን ክፉ ነገር ለእነሱ መልካም በማድረግ መልሱት ፤ በፍጹም ክፉ ነገር በማድረግ አትመልሱ ፡ በሃሳባችሁም ቢሆን ክፉ ነገሮች መልሳቹ ስለማድረግ አታስቡ፡፡ አምላክ ፀጋና ክብር ከእናንተ ጋር ይሁን ፤ ”

   በእነዚህ የማህበራዊ መድረኮች ሊያገኙኝ ይችላሉ ፤