10 Apr 2026, Fri

“ጥቅም” የነገሰበት ዓለም

ዛሬ በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ‘ሰው’ መሆን እንደ ፋራነት፣ ‘አስመሳይ’ መሆን ደግሞ እንደ ስልጣኔ የሚቆጠርበት የተገላቢጦሽ ዘመን ላይ ደርሰናል ። ኪስህ ሞልቶ ህሊናህ ከጎደለ፣ አንተ ሀብታም ሳይሆን ‘ድሃ’ ነህ ። በየመንገዱ የምታገኘው ሰው ሁሉ ፈገግ የሚልልህ ወድዶህ ሳይሆን፣ ያንተ ‘ጥቅም’ ስላጓጓው መሆኑን ስትረዳ የጭሰኛው እውነት ይገባሃል ።

1. የጥቅም እንጂ የህሊና ጓደኛ የለም! 💰🐍

ድሮ ጓደኝነት ‘ለአጥንት’ ነበር፤ ዛሬ ግን ‘ለኪስ’ ሆኗል ። ስትሞላለት አጃቢህ፣ ስትጎድልበት ግን አላፊህ የሚሆኑ የጥቅም ሰንሰለቶች በዝተዋል። ወዳጄ… መቶ አጃቢ ከሚኖርህ፣ አንድ የቁርጥ ቀን ‘ሰው’ ይኑርህ ። በፌስቡክ በቲክቶክ ላይ ‘ላይክ’ (Like) የሚያደርጉህ ሺዎች ቢሆኑም፣ ስትወድቅ እጃቸውን የሚዘርጉልህ ግን ከጣት አይበልጡም ። ለሰው ሳይሆን ለጥቅም የሚሰግድ ትውልድ መካከል ነን ።

2. የታሸገ ውበትና የባዶነት ህይወት! 💅🚫

የዘመኑ ሰው ውበቱን ‘ፓኬጅ’ (Package) ላይ አደረገው፤ ውስጡ ግን ባዶ ቅርፊት ነው ። በውሸት ፀጉር፣ በፕላስቲክ ጥፍርና በሜካፕ የታሸገ ውበት ይዘሽ ‘ንግስት ነኝ’ አትበዪኝ ። ውበት ህሊና ላይ ካልጀመረ፣ ፊት ላይ ያለው ኬሚካል ዝናብ ሲመጣ ይሟሟል ። ስልጣኔ ማለት ራስን መካድ ሳይሆን፣ ማንነትን አውቆ በኩራት መኖር ነው ። የውሸት ህይወትህን ለሰዎች ለማሳየት ስትለፋ፣ እውነተኛ ማንነትህን አጥተኸዋል ።

3. የላይክ (Like) ባሪያና የሰላም ድሃ! 📱📉

ለሰዎች ‘እዩኝ’ ስንል የራሳችንን ሰላም ቀበርነው ። የምንበላውን ምግብ የምንመርጠው ለጣዕሙ ሳይሆን ፎቶው ፌስቡክ ቲክቶክ ላይ እንዲያምር ነው ። የምንሄድበትን ቦታ የምንመርጠው ለደስታችን ሳይሆን ለሰዎች ‘እዩኝ’ ለማለት ነው ። በሰው እይታ ውስጥ ለመኖር ስንሮጥ፣ በራሳችን ህይወት ውስጥ ‘ባዕድ’ ሆነን ቀረን ።

የጭሰኛው መልእክት ⛔️⚠️

ወዳጄ… ሰውን በሰውነቱ እንጂ ለኪሱ ብለህ አታክብረው ። ራስህን ለሰዎች ለማስደሰት ብለህ ማንነትህን አትሽጥ ። ዓለም በውሸት ስትሰክር ፣ አንተ በእውነት ‘ናውዝ’ ። በሚያልፍ ጥቅም የማያልፍ ጠባሳ በህሊናህ ላይ አታኑር ።

📢 ይህ እውነት የህሊናህን በር ካንኳኳው፦

✅ ለእውነተኛ ‘ሰው’ እና ለሞራል ዋጋ ካለህ Like አድርግ!

✅ አስመሳይነትን እንዲገፈፍ ለወዳጅህ Share በማድረግ እሳቱን አቀጣጥለው!

ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *