በጃፓን ገር ልጆች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብተው መደበኛ ትምህርት መማር ከመጀመራቸው በፊት በመጀመሪያዎቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ የሞራል እሴቶችን ፣ ትብብርን እና ማህበራዊ ሃላፊነትን እንዲማሩ ይደረጋል።
በነዚህ አመታት ውስጥ ልጆቹ ፡-
፩. በክፍል ውስጥ ተቀምጠው መደበኛ ትምህርት ተምረው በወረቀት ፈተና ተፈትነው ውጤታቸው ተገምግሞ በደረጃቸው አይለኩም ፤ እውቀታቸው የሚለካው መማር በልምድ ላይ የተመሰረተ ነው።
፪. የመማርያ ክፍሎቻቸውን ያጸዳሉ፣ ምሳ ለሌሎች ሰዎች እንዲመግቡ ይደረጋሉ፤ አንድ የተመረጠ ሃሳብ ቀርቦላቸው በዚያ ሃሳብ ላይ የራሳቸውን አስተያየት እንዲያንፀባርቁ ይደረጋል፡፡
፫. ግጭቶችን እንዴት መፍታት እንዳለባቸው፣ ስለ አክብሮት ማሳየት እና ለቡድን እንዴት ሃሳብ ማበርከት እንዳለባቸው እንዲማሩ ይደረጋል።
የጠንካራ ሞራል ፣የመልካም ሥነ-ምግባር እና የትብብር አስተሳሰብ ከገነቡ በኋላ በ9 ወይም 10 ዓመታቸው ተማሪዎቹ ይበልጥ ጥብቅ የሆኑ አካዳሚያዊ ጉዳዮችን መፍታት እንዲችሉ ትምህርት መማር ይጀምራሉ፡፡
ጃፓኖች የወደፊት ዜጋን መቅረጽ በፈተና ውጤቶች ላይ የተመሰረት ብቻ ሳይሆን ጠንካራ የሞራል ፣የመልካም ሥነ-ምግባር እና የትብብር አስተሳሰብን መገንባትንም ያካተተ መሆን አለበት ብለው ያምናሉ፡፡
እናንተስ ስለ ሀገራቹ የትምህርት ስርዓት ምን ትላላቹ ?
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza
