10 Apr 2026, Fri

ከሮጣቹ አይቀር ለወርቅ ሩጡ ፤

ፕሮፌሰሯ ከዚህ በፊት ለተማሪዎቿ ብዙ ጊዜ ፈተናን ፈትናቸው ታውቃለች፡፡ አንድ ጊዜ ግን ከዚህ በፊት አድርጋ የማታውቀውን ነገር ለማድረግ ወሰነች፡፡

ለፈተና ተዘጋጅተው የፈተናው ወረቀት እጃቸው አስኪገባ የሚጠባበቁትን ተማሪዎች እንዲህ አለቻቸው፣

“ይህንን ፈተና ሳልፈተን የ“B” ውጤት ቢሰጠኝ በደስታ እቀበላለሁ” የምትሉ ተማሪዎች ስማችሁን እየተመዘገባችሁ አሁኑኑ ከዚህ ክፍል መውጣት ትችላላችሁ፡፡

“ፈተናውን መፈተንና “A” ለማግኘት ስለተዘጋጀሁ፤ ጥረት አደርጋለሁ።”የምትሉ ተማሪዎች እነሱ ከወጡ በኋላ ፈተናውን ትወስዳላችሁ።”

ይህን ሃሳብ እንደተናገረች ከተማሪዎቹ አብዛኛዎቹ ስማቸውን እያስመዘገቡ ክፍሉን ጥለው ውልቅ አሉ፡፡

እጅግ የተገረመችው አስተማሪ፣ አሁንም መውጣት የሚፈልግ ተማሪ ካለ በሚል አንድ የመጨረሻ እድል ሰጠች፡፡

ይህንን የመጨረሻ እድል ገና ከአንደበቷ ከማውጣቷ ከአንድ ተማሪ በስተቀር ተማሪው ሁሉ ስሙን እያስመዘገበ አንድ በአንድ ተፈተለከ፡፡

መውጣት የፈለጉት ተማሪዎች ሁሉ መውጣታቸውን ካረጋገጠች በኋላ “A” ለማግኘት እፈተናለሁ ብሎ የተዘጋጀውን ብቸኛ ተማሪ አንድን ደስ የሚያሰኝ ዜና አበሰረችው፣

“አንተ አሁኑኑ፣ ፈተናውን ሳትፈተን “A” ተሰጥቶሃል – ፈተናውን ስለተፈተንክ ሳይሆን ስለተዘጋጀህ፡፡ “A” የሚገባህ ያንን ለማግኘት የቆረጠ ማንነት ስላለህና ለዚያም ውስጥህን ስላዘጋጀህ ነው!!!” አለችው

👉 ከደረስንበት ይልቅ የተሻለ ደረጃ እያለ፤ “የደረስኩበት ይበቃኛል” በማለት መስከን ለምንድን ነው?

👉 ለወርቅ መሮጥ ሲቻል ለብርና ለነሃስ መሮጥ ለምንድን ነው?

በደረስንበት ከረካን ወዳልደረስንበት የተሻለ ነገር ለመራመድ ፈቃዱም አይኖረን፡፡

የእምቅ ብቃታችን ጠላት ምንድን ነው ?

የለመድነው፣ የተመቸን፣ የማያስለፋን፣ ሁሉም ያደረገው፣ “መኖር ከተቻለ ምን አስለፋኝ” ያሰኘን አይደለምን?

ነገር ግን፣ ከዚህ የተሻለ አለ!!!

👉 ራስህን ካዘጋጀህ፣ ብዙም ሳትቆይ አሁን ከደረስክበት የተሻለ ደረጃ እንዳለ ማየት ትጀምራለህ፡፡

👉 ሰው ከጻፈው አንተ ማንበብ ትችላለህ፣ ሰው ካሰረው አንተ መፍታ ትችላለህ፣ ሰው ከደበቀው አንተ ማግኘት ትችላለህ፡፡

“ለአማካኝና ለመካከለኛ ውጤት ለሰከኑ ሰዎች አማካኝና መካከለኛ ውጤት እንደ ግሩም ውጤት ይቆጠራል” – Unknown Source

👉 ማወቅ ሲቻል ሰው ባለማወቅ ለመኖር ሲመርጥ ያስገርማል፡፡

👉 መቶ ማግኘት ሲቻል ሰው በሃምሳ መስከኑ ግር ይላል፡፡

ከዚህ የተሻለ ማድረግ ስችል እስካሁን ባደረኩት የመስከኔ ምንጩ ምን እንደሆነ አግኝቼው እስክቀርፈው ድረስ ሕይወት ባሉበት መርገጥ ይሆናል፡፡

👉 መድረስ የምትችለው እስካሁን ከደረስክበት ደረጃ ያለፈ እንደሆነ በምን ታውቃለህ?

👉 ማወቅ የምትችለውስ እስካሁን ካወከው እውቀት የላቀ እንደሆነ ምን ማረጋገጫ አለህ?

👉 ማንነትህን መድረስ እስከሚችልበት ደረጃ ድረስ ወጥረኸዋል?

👉 በአማካኝ ውጤት ለማለፍ ነው የምትሄደው ወይስ የብቃትህ ጥግ ድረስ ለመድረስ?

👉 አሁን ያለህበት የትምህርት ደረጃ ላይ ለምን አቆምክ? አሁን የደረስክበት ደረጃ ላይስ ለምን ሰከንክ?

አስተውል !

👋 ሕይወት ግሩም የሆኑ እድሎችን የምትሰጠው ለተዘጋጁት ነው፡፡

👉 ስኬታማዎቹ ሰዎች እድለኞች ስለሆኑ አይደለም ሁኔታው የሚመጣላቸው ፣ ስለተዘጋጁ እንጂ፡፡

👉 የስራ እድል ለእድለኞች አይደለም ተምረው ለተዘጋጁ እንጂ !

👉 የሩጫ ውድድር የሽልማት እድል ለእድለኞች አይደለም፣ በሩጫ ልምምድ ለተዘጋጁ እንጂ!

💪 በአንድ ነገር ራስህን ብቁ በማድረግ ስትዘጋጅ መልካም እድለኛ ለመሆን ወሰንክ ማለት ነው፡፡

ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *