10 Apr 2026, Fri

ይህ አባባል ቀላል ቢመስልም ጥልቅ ትርጉም ይዞል ፤ ሰው ህይወቱን እንዴት ሊመራ እንደሚችል የሚያስተምር ነው። ህይወታችን በሦስት ዘመናት ተከፍላለች ፡ ትናንትዛሬ እና ነገ። እያንዳንዱም ቀን የራሱ መልዕክት እና ትምህርት አለው።

ትናንት ያለፈ ነው ፤ የማይመለስ ፤ ልንቀይረው የማንችለው ጊዜ ነው። በትናንት ደስታ ነበር ፣ ስኬት ነበር ፡ እንዲሁም ስህተትና ህመም ነበር። ብዙ ሰዎች በትናንት ይኖራሉ ፤ “ ባይሆን ኖሮ ” ብለው ይፀፀታሉ ወይም ያለፈውን ትላንት ባገኙት ድል (ደላቸውን) ብቻ ተመልክተው ዛሬን ይዘነጋሉ። ነገር ግን ትናንት የሚሰጠን ነገር አንድ ነገር ብቻ ነው እሱም ትምህርት ነው። ከስህተታችን መማር እንጂ በእሱ መኖር አይጠቅመንም።

ዛሬ ያለን እውነተኛ ሀብት ነው። ዛሬ መውሰን እንችላለን ፣ መጀመር እንችላለን ፣ መቀየርም እንችላለን። ህይወት ዛሬ ይኖራል ፡ በዛሬ ህይወትን ለመኖር ደግሞ ተግባርጥረት እና ውሳኔ ማድረግ ድግሞ ከእኛ የሚፈልግብን ጊዜ መሆናችንን ማወቅ መቻል ምንኛ መታደል ነው። ትናንት ምን እንደነበር ሣይሆን ፡ ዛሬ በርትተን ለነገ ምን እንደምንሆን ማወቅ ወይም መተንበይ ነው ወሳኙ ነጥብ። ዛሬ ላይ የወደፊታችንን ካየንና ላየነው ነገ ዛሬን በደንብ በሙሉ ኃይል ለማሳካት ማድረግ ከጀመርን ህይወትን ዛሬ ላይ እየኖር ነው ብለን ብናስብ ምክንያታው ነን። ዛሬን በሙሉ መኖር ማለት ህልማችንን ትናንት ከነበርንበት ዛሬ ላይ አንድ እርምጃም ቢሆን ወደ ህልማችን መቅረብ እንድንችል መሥራት መቻል ማለት ነው።

ነገ ያልመጣ ነው ፤ ዋስትና የለውም ግን ተስፋ ይዞ ይመጣል። ነገ ማለት የምፈልገው ፡ እንዲኖረን የምንመኘው ህይወት ዛሬ በምንዘረጋው ገመድ ይመሰረታል። ሰው ሁሉ ለነገ ህልም አለው ፡ ነገር ግን ያ ህልም እውን የሚሆነው ዛሬ ሲሰራበት ብቻ ነው።

ስለዚህ ህይወት ሶስት ቀን ናት ሲባል ፡

ትናንትን እንደ ትምህርት ውሰድ ፣

ዛሬን እንደ ዕድል እቀፍ ፣

ነገን እንደ ተስፋ ጠብቅ ።

በትናንት አንገዛ ፣ በነገ አንዘገይ ፤ ዛሬን እንኑር። ዛሬን እንሥራ ፣ ዛሬን እንቀየርበት። “እውነተኛ ህይወት ዛሬ ይጀምራል።”

ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *