10 Apr 2026, Fri

በአልጋ ላይ በሞት አፋፍ ላይ የነበሩ አንድ አዛውንት ለሀኪማቸው እንዲህ ሲሉ ጨዋታቸውን ጀመሩ ፡

“ሀኪም ሆይ አትጨነቅ ፤ እንደምሞት አውቃለሁ።

እዚህ መምጣት አልፈለኩም ነበር ግን እነሱ አመጡኝ።
እባክህን ስለእኔ አትጨነቅ ፡ ፀጉሬን ተመልከት ፣ የለም። እኔ በጣም አርጅቻለሁ አንተ ግን ወጣት ነህ። ከህይወት ብዙ ተምሬያለሁ ፡ ቅር ካላለህ ከመሞቴ በፊት ጥቂቶቹን እነግርለሁ።”

  • የ፬ ዓመት ልጅ እያለሁ ዓለም የእኔ እንደሆነች አስብ ነበር።
  • ፲፬ ዓመት ሲሞላኝ ዓለምን መግዛት ፈለኩ ፤ በምድር ላይ ከኖሩ ታላላቅ ሰዎች አንዱ እሆናለሁ ብዬ አስብ ነበር።
  • ፳፪ ዓመት ሲሞላኝ ትልቁ ባለጸጋ መሆን ፈለኩ።
  • ፳፭ ዓመት ሲሞላኝ ፍቅረኛ መያዝ ፈለኩ
  • ፵ ዓመት ሲሞላኝ ለሁሉም ጠቃሚ መሆን ፈለኩ።

“አሁን እዚህ ስሆን መሞት እፈልጋለሁ።
እንግዲህ በብዙ ጊዜያት ብዙ ነገሮችን ፈልጌ ነበር።

ከሁሉም በላይ ደግሞ ደስተኛ መሆን ፈልጌ ነበር ፤ ደስተኛ ለመሆን ምርጡ መንገድ ሌሎችን ማዳመጥ ነው ብዬ አስብ ነበር።”

“ዩኒቨርሲቲ ስገባ የእንስሳት ጥናት (Zoology) መማር ፈልጌ ነበር ነገር ግን ሁሉም ሰዎች ኢንጂነሪንግ እንድማር ነገሩኝ ምርጥ ኢንጂነር እንደምሆን ነገሩኝ ፤ ስለዚህ እነሱን አዳመጥኩ።

የትምህርት ክፍያዬን የሚከፍልልኝ ሰው አልነበረኝም ፡ መስራት እና ክፍያዬንም መክፈል ነበረብኝ።

በሶስተኛ ዓመቴ ከትምህርቴ ጋር መጣጣም አልቻልኩም ፡ ማቋረጥ ነበረብኝ።
ስተወው እነዚሁ ሰዎች “የእንስሳት ጥናት መማር ነበረብህ ! ” አሉኝ።

  • ፳፰ ዓመት ሲሞላኝ ሁሉም ማግባት እንዳለብኝ ነገሩኝ።
    ሚስት እንደሚያስፈልገኝ ነገሩኝ ፤ ስለዚህ እነሱን አዳመጥኩ አገባሁ።
    ትዳሩን ከጀመርን ከ6 ዓመት በኋላ ባለቤቴን ከጎረቤቴ ጋር ተኝታ ያዝኳት።
    ለምን ብዬ ጠየቅኳት እሷም በጥፊ መታችኝ ፤ ተናደድኩኝ እና ምንም አላልኩም።
    በሚቀጥለው ቀን ከስራ ስመለስ ልጆቼን ይዛ ሸሽታ ነበር ፡ አሁን ብቸኛ ሆኜ እየሞትኩ ነው።
  • “በ፵ ዓመቴ ትልቅ ኮንትራት ሥራ አገኘሁ ፡ ስሜ በዜና ላይ ወጣ።

በሚቀጥለው ቀን ሁሉም ጓደኞቼ እና ቤተሰቦቼ ቤቴ ነበሩ ሁሉም ከባድ ችግር እንደነበረባቸው ነገሩኝ። በአንድ ሣምንት ውስጥ ገንዘቡን እንመልሳለን በሚል ቃል ስለገቡ ለእነሱ ሰጠኋቸው።

ነገር ግን ቃል እንደገቡት ገንዘቡን ለመመለስ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ኮንትራቱን ማጠናቀቅ አልቻልኩም ስለዚህ ለ6 ዓመታት ታሰርኩ።

እስር ቤት ቆይቼ ወጣሁ። ስወጣ እነዚያ ሰዎች በአጠገቤ አልሆኑም አልነበሩም።”

“በዚህ ሁሉ ጊዜ የሰራሁት አንድ ስህተት አለ ፡ አሁን ለእኔ ግልጽ የሆነልኝ ነገር ባካፍልህ ደስ ይለኛልና ልንገርህ።

ራሴን ለማዳመጥ ፈቃደኛ አልነበርኩም ፤ የራሴን ማንነት ችላ ብዬ ሌሎችን አዳምጥ ነበር ፤ አሁን እዚህ ስሆን ከእኔ ጋር ያለው ብቸኛው ሰው ራሴ ነኝ።”

“እንግዲህ ሌሎችን ማዳመጥ በጣም ጥሩ ነው ፤ ከሌሎች ምክር መጠየቅ በጣም ጥበብ ነው ፤ ነገር ግን የራስን ማንነት ችላ ማለት በጣም አደገኛ ነው።

ለልብህ ትኩረት ለመስጠት እምቢ ማለት በጣም በጣም አደገኛ ነው።”

“ዛሬ ማታ ወደ ቤትህ ስትደርስ ቁጭ በልና አንድ ብርጭቆ ውሃ ጠጣ።
ከፈለክ አይንህን ጨፍን ወይም ከፈለክ ክፈተው ከዚያም ከራስህ ጋር ተነጋገር ከራስህ ጋር ተከራከር።
ብቻህን መንገድ ላይ መሄድ እና ስትራመድ ከራስህ ጋር ማውራት መጀመር ትችላለህ።”

ራስህን ሊሽር የሚችለው ብቸኛው እውነተኛው አምላክ ነው ፤ ከእውነተኛው አንዱ አምላክ ቀጥሎ ራስህን አዳምጥ። አሁን ለአንተ ትርጉም ላይሰጥ ይችላል ነገር ግን ሁልጊዜ የነገርኩህን አስታውስ ራስህን ማዳመጥን ተማር።

ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *