ብዙ ሰዎች ቀናቸውን የሚጀምሩት ስልካቸውን በመነካካት ወይም የሌሎችን ሰዎች ወሬ በመስማት ነው። ነገር ግን ሳይንሱ የሚለው ሌላ ነው!
ለምን ይህች ሰዓት ወሳኝ ሆነች ?
ጠዋት ስትነቃ አንጎልህ “Theta State” በሚባል ሞገድ ውስጥ ነው የሚቆየው። በዚህ ሰዓት አንጎልህ ልክ እንደ ስፖንጅ ነው፤ ያገኘውን መረጃ ሁሉ ያለምንም ማጣሪያ በቀጥታ ወደ Subconscious Mind (ከንቃተ ህሊና በታች ያለው አእምሮ) ይልከዋል።
በዚህ ሰዓት ስልካችሁን ስትከፍቱ አንጎላችሁን ለቀኑ ሙሉ “ጭንቀት” እና “የሌሎችን ሕይወት መቃኘት” ውስጥ እየከተታችሁት ነው።
√ ምስጢሩን ለመጠቀም እነዚህን 3 ነገሮች አድርጉ፦
• ስልክህን ለ1 ሰዓት አርቀህ አቆይ፦ አንጎልህ ለቀኑ ሙሉ “ተቀባይ” (Reactive) ሳይሆን “ፈጣሪ” (Creative) እንዲሆን ዕድል ስጠው።
• ለራስህ “Software” ስጥ፦ በዚያች የመጀመሪያ 1 ሰዓት ውስጥ መጽሐፍ አንብብ፣ እቅድህን አውጣ፣ ወይም ስለ ወደፊት ስኬትህ አስብ። አንጎልህ በዚያ ሰዓት የምትነግረውን ሁሉ እንደ ትዕዛዝ ይቀበላል።
• የምስጋና ጊዜ፦ ስለ አለህ ነገር አመስግን። ምስጋና በአንጎልህ ውስጥ “Dopamine” እና “Serotonin” እንዲመነጭ በማድረግ ቀኑን ሙሉ በደስታ እንድትቆይ ያደርግሃል። የመጀመሪያዋ የጠዋት 1 ሰዓት የሙሉ ቀኑን 70-80% ስሜት ትወስናለች። አንጎልህን በቆሻሻ መረጃ አትሙላው፤ ይልቁንም ለታላቅነት አዘጋጀው።
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza
