ድሮ ትዳር “ቅዱስ” እና የነፍስ ውህደት ነበር ። አሁን ግን ትዳር “ንግድ ኢንቨስትመንት” (Investment) ሆኗል። ሴቷ የባንክ ደብተር ታያለች፤ ወንዱ የመልክ ማራኪነት ይለካል። ፍቅር ? እሱማ ድሮ በነ አያቶቻችን ዘመን ቀረ ! ዛሬ ጥቅም ባለበት ፍቅር አለ፤ ጥቅም ሲያልቅ ግን ፍቺው ቀዳሚ ይሆናል ።
የጥሎሽ ገበያና የ6 ወር ትዳር ![]()
ሰርግ ሲታሰብ የሚወራው ስለ ፍቅር ሳይሆን ስለ ወጪ ነው። ወጣቱ ገና ትዳር ሳያስብ የሰርጉ ወጪና የሆቴሉ ድግስ ያስጨንቀዋል። ለአንድ ቀን ጭብጨባና ለሰዎች እይታ ተብሎ የሚገባ የ10 ዓመት ብድር መጨረሻው ኪሳራ ነው። የሚገርመው ያ ሁሉ ተደግሶና ተበልቶ፣ በስድስት ወር ውስጥ “አልተስማማንም” በሚል ሰበብ ይፋታሉ። ምክንያቱም ትዳሩ የተመሰረተው በፎቶና በቪዲዮ ላይ እንጂ በመግባባት ላይ አይደለም ።
የስፖንሰር ፍለጋና የመልክ ምርጫ ![]()
እህቴ ሆይ… እውነት እንነጋገር፤ ወንድን እንደ “ኤቲኤም” (ATM) ማየት መቼ ነው የምታቆሙት? “የምወደው ሰው ደሃ ነው” ብለሽ ትተሽው፣ የማትወጂውን ሀብታም ስታገቢ በገንዘብ የተገዛ ትዳር ገንዘቡ ሲያልቅ አብሮ እንደሚያልቅ አታውቂም? ወንዶችም ብትሆኑ ሴትን እንደ ዕቃ ወይም እንደ “የቤት ጌጥ” አትዩ። ውበት ይረግፋል፣ መልክ ይጠወልጋል፤ የሚቀረው ግን አብሮ አደግነትና መከባበር ብቻ ነው ።
የቲክቶክ ቪዲዮና የውሸት ጥንዶች ![]()
አሁን አሁን መፋታት “ዘመናዊነት” እየሆነ መጥቷል ። ሶሻል ሚዲያ ላይ የምናያቸው “የውሸት ጥንዶች” (Couples) የትክክለኛውን ትዳር ትርጉም አበላሹት ። “እከሌ ሚስቱን ዱባይ ወሰዳት፣ አንተ ግን ሱሉልታ አልወሰድከኝም!” የሚል የፉክክር ኑሮ ቤትን ሲኦል ያደርገዋል ። ትዳር ማለት የታመመ መጠየቅ፣ የተራበ ማጉረስና የወደቀን ማንሳት እንጂ የቲክቶክ ትዕይንት አይደለም ።
ወጣቱ ሆይ… አትፍራ፤ ትዳር ከባድ ቢሆንም ጣፋጭ ነው። ግን ስታገባ ለሰው፣ ለገንዘብ ወይም ለመልክ ብለህ አታግባ ። ለፍቅርና ለመግባባት ብለህ አግባ ። ቤትህን በሲሚንቶ ሳይሆን በፍቅር ገንባው፤ ያኔ ንፋስ ቢመጣ አይፈርስም ።
የቲክቶክ “ገለባ” ሰለቸን እኮ፤ ቁም ነገር እናውራ !
ይህ እውነት የህሊናህን በር ካንኳኳው፦
• ለእውነተኛ ፍቅርና ለትዳር ክብር ዋጋ ካለህ Like አድርግ።
• ትውልዱ ከጥቅም ትስስር እንዲወጣ Share በማድረግ እሳቱን አቀጣጥለው።
• ለተጨማሪ የህሊና ወጎችና የጭሰኛው ፍልስፍና ገጻችንን Follow ያድርጉ ።
ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
http://t.me/danelroza
ለፌስቡክ
👇👇👇
http://fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇👇👇
linkedin.com/in/danelrozlroza
