Christopher Nolan በ Inception ፊልሙ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል። የ ኖላን ዋና ገፀባህሪ “Dominick / Dom” {ተዋናዩ ዲካፕሪዮ} የሰዎች ህልም ላይ ወረራ ያካሂዳል ፣ ሃሳብ ይሰርቃቸዋል ሲለያቸው ሌላ ሃሳብ ኢምፕላንት አድርጎባቸው ነው። ያ የተተከለባቸው ሃሳብ የሱ ይሁን የ ትውስታቸው መለየት አይችሉም እናም ይታለላሉ።
ኖላን የኢማጅኔሽን መብቱንና ብቃቱን ተጠቅሞ ኢንሰብሽንን ሲሰራ እነዚህ ሁለት የስነልቡና ህልዮቶች ለሃሳቡ ኮንክሪት መሰረት ነበሩ።
① Fruedian Dream Psychology
ፍሮይድ 1900 ላይ ፍካሬ ህልምን ሲፅፍ ተቀባይነት የነበረው ሃሳብ አልነበረም። 600 ኮፒ በስምንት አመት ውስጥ መጨረስ አልቻለም ነበር። ኋላ ላይ ያ ተቀይሯል።
ህልም ኢ ንቅ የሆነውን የአዕምሮ ክፍል ለመድረስና ለመበርበር Royal Road መሆኑን ይነግረናል። ህልም ንቅ የሆነው የአዕምሮህ ክፍል “የጨቆናቸው” ሃሳቦች አርነት ነው። ያ አርነት አውዶቹን እንድታርም፣ እንድጨምርና እንድትቀንስ ይረዳሃል።
ለምሳሌ ራሱ ፍሮይድ የሳኪያትሪ እገዛ ስትወስድ የነበረች ታካሚው አለመሻሻልን ተከትሎ በጥፋተኝነት ስሜት ይታመስ በነበረበት ባንደኛው ጊዜ ምሽት ላይ ህልም ያያል። በህልሙ ውስጥ ታካሚዋ የምትወስዳቸውን መድሃኒቶች በማየት ለአለመሻሻሏ ምክኒያቱ የተበከለ ስሪንጅ መጠቀሟ መሆኑን ያረጋግጣል። በዚህ ይነቃል። ይሄ ከላይ ያነሳሁልህን “wish fulfillment” ግልፅ ያረግልሃል።
በህልምህ የምታየው በእውኑ አለም ተከስቶ የምታስታውሰው መረጃ manifest content ሲሆን የህልም ፍቺና ትርጉም የሚገኘው ደግሞ distort የተደረገው ወይም የታረመና የተስተካከለ የተነካካው latent content ላይ ትኩረት በማድረግ ነው። ፍሮይድ በዚህ መልኩ የሰዎች ኢ–ንቅ የሆነው የአዕምሮ ክፍልን access በማድረግ ክሊኒካል ሳይኪያትሪ ያካሂድ ነበር።
ይህ ቲየሪ ላቅ ያለ ፋንታሲን ተላብሶ በፊልሙ ተንፀባርቆ ይታያል። ያለዚህ ህልዮት የፊልሙን መሰረታዩ ማጠንጠኛ ሃሳብ ማሰብ ከባድ እንደሚሆንም እናምናለን።
② White Bear effect/ Ironic Process Theory
ሁለተኛው ሃሳብ : “ለሌሎች ህልም ማበጀት” ነው። ለሃሳቡ ክሬዲት ዶስቶቪስኪን እንጠቅሳለን።
“አምዕሮህን የዋልታ ድብ እንዳያስብ ብታደርገው ያ የተረገመ ነገር በየደቂቃው ወደ አዕምሮህ ይመጣል። “
(Try to pose for yourself this task: not to think of a polar bear, and you will see that the cursed thing will come to mind every minute.”) በሚል
“Winter Notes on Summer Impressions (1863) ላይ ባወጣው አርቲክል ፅፎ ነበር።
ከአንድ ምዕተአመት በኋላ በ1987 ሶሻል ሳይካለጂስቱ Daniel Wegner “Ironic Process Theory ” ወይም ” “White Bear effect” የሚባል ቲየሪ ነደፈ። ቲየሪው የተደገፈው በጥናት ነበር። Wegner ተሳታፊዎችን ስለ ድብ እንዳያሳቡ ያሳስባቸዋል። ተሳታፊዎቹ ግን ደጋግመው ያንን በማሰብ ተጠምደው ተገኝተዋል። በአጭሩ ሲደመደምም ማንኛውም በንቅ አዕምሮ ላለማሰብ “የጨቆንናቸው” ሃሳቦች ደጋግመን እንድናስባቸው ይሆናሉ።
ይሄ ሃሳብ ደጋግሞ Inception ውስጥ ተንፀባርቋል ወይም ኖላን በሚገባ አዳብሮና ፋንታሲ አላብሶ አምጥቶታል።
ለምሳሌ ቀጣዩ ቃለ-ተውኔት አርተር በሳይቶ ጭንቅላት የሚፈበርከው ሃሳብ ከላይ ላነሳነው ማሳያ ይሆናል።
👉 Saito: If you can steal an idea, why can’t you plant one there instead?
👉 Arthur: Okay, this is me, planting an idea in your mind. I say: don’t think about elephants. What are you thinking about?
👉 Saito: Elephants?
👉 Arthur: Right, but it’s not your idea!!!
