የአወቁ ሰዎች ሁሉ ያረጁ ወይም የተማሩ ላይሆኑ ይችላሉ ፡ የተማረ ወይም ያረጀ ሁሉ ያወቀ ላይሆን ይችላል።
የአዋቂነት መለኪያው በማዕረግም በእድሜም ላይሆን ይችላል ፤
ታዲያ አዋቂነት እንዴት ይገኛል ? እንዴትስ ይገለጣል ?
ከበሽታው በላይ መድሃኒት ከጨለማው በላይ ብርሃን መሆን ነው ፡ ትልቅነትም እሱ ነው ፤ ፈዋሽ እና ብርሃን መሆን ነው ፡ ከህመም ማዳን ከጨለማ ማውጣት።
አዋቂዎች እንደ እህል ዘር ናቸው ከተበሉ የሚያጠነክሩ የሚያድኑ ናቸው ፤ መሬት ከነኩም የሚበቅሉ የሚበዙ ናቸው ።
እንደ አረም የትም አይበቅሉም እንክብካቤ ይፈልጋሉ።
