12 Dec 2025, Fri

ንግድ ከመጀመርህ በፊት እነዚህን ክኒኖች ዋጥ ፤

💊 ቤተሰብህም ቢሆን ማንም ለዕዳህ ኃላፊነት
      እንደማይወስድልህ አስበህ ተዘጋጅ ፦

ጓደኞችህ ስለሚያውቁህ ብቻ ከአንተ እንዲገዙ ፣ ቤተሰብ እንዲያበረታታህ ወይም እንዲያስተዋውቅ አትጠብቅ።

አብዛኛዎቹ የመጀመሪያ ደንበኞችህ እንግዳዎች ይሆናሉ ፤ እንግዶች ባልፈው ነገርህ ላይ ሳያተኩሩ ስለምታቀርበው ዋጋ ያስባሉ ፤ እነሱ ችላ ሊሉህ የማይችሉትን ጥሩ ነገር በመገንባት ላይ አተኩር።

💊 በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ጠንክረህ ሰርተህም ላታተርፍ እንዲያውም ልትከስር ትችላለህ ፦

በአብዛኛው ይህ የሚገጥምህ ንግድህ እስከሚረጋጋ ድረስ ነው። ነፃነት ነፃ አይደለም ፤ ላብህን ትከፍልበታለህ።

💊 በንግድ ውስጥ የገንዘብ ችግሮች እንዳሉ እንወቅ ፦

በገንዘብ አያያዝህ ቸልተኛ ከሆንህ በንግድ ውስጥ ያልጠበቅኸው ከፍተኛ ዕዳ ሊመጣብህ ይችላል።

የገንዘብ ፍሰት አስተዳድርን ፣ በጀት ማውጣትን ፣ ለታክስ መቆጠብ እና ትርፍን እንደ ደሞዝ የመመልከት ፍላጎትህን መቃወም መማር ያስገፈልግሃል።

ገበያ የሚቀዘቅዝባቸው ወራት ፣ ከደንበኞች የሚዘገዩ ክፍያዎችና ድንገተኛ ወጪዎች ይኖራሉ ፤ ንግድ የገንዘብ አያያዝ ጥሩ ልምድ ይጠይቃል።

💊 የንግድ መክሊት በቂ አይደለም ፤ መዋቅር (system) ያስፈልጋል ፦

የንግድ ተሰጥኦና ጥሩ ሀሳቦች አሉኝ ልትል ትችላለህ።

የአሰራር ሂደቶች ፣ የስራ ፍተሻ ዝርዝሮች ፣ የጊዜ መርሐግብር ዘዴዎችና ውክልናዎች ያስፈልጋሉ ፤ እነዚህን ስትጠቀም በታመምህበት ወይም በእረፍት በወጣህበት ቀን ንግድህ አይፈርስም።

ምርጥ ንግዶች በአዋቂነት ብቻ ሳይሆን በመዋቅር ጭምር ይሰራሉ።

💊 ንግድ የማንነትህን የእያንዳንዱን ክፍል ይፈታተናል።

ባለጌ ደንበኞች ፣ ስራህን አመሳስለው የሚሰሩ ሌሎች ነጋዴዎች ፣ የገንዘብ እጥረት ፣ የማይጠቅሙና ክፉ ሰራተኞች ፣ የተበላሹ ሽርክናዎች ፣ ከባድ ውሳኔዎችና ጥርጣሬዎች ይፈታተኑሃል።

ንግድህን ለመገንባት እነዚህን የመፍታት ችሎታህን አዳብር ፤ የበለጠ ጠንካራ ፣ ብልህ ፣ ስነስርዓትህ የተሞላ ፣ ትኩረት ያለህና ስልታዊ መሆን ያስፈልግሃል።

ንግድ መጀመር በህይወት ውስጥ ጠቃሚ ከሆኑት መንገዶች አንዱ ነው ፤ ነገር ግን አቋራጭ መንገድ አይደለም።

ውጣ ውረዶች እንዳሉት ማወቅ ያስፈልጋል።  ይዘረጋል ፣ ይሰብራል ፣ ያድሳል ፤ ንግድ እንደ ጦር ሜዳ እምነትህን ይፈትሻል።

አቅማችንን እንፈትሽ ፤ በእውቀት እንደግ ፤ ያገኘነውን እውቀት በተግባር በማዋል እንፈትሸው ፤ በዕውቀት ለማደግ አዘውትረን እናንብብ።

ይቀላቀሉ ለቴሌግራም
👇👇👇
t.me/danelroza
ለፌስቡክ 
👇👇👇
Fb.com/danelroza
ለሊንክደን ፡
👇🏾👇🏾👇🏾
linkedin.com/in/danelroz

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *