13 Dec 2025, Sat

ተስፋ ቆርጠሀል ? አንዴ ረጋ ብለህ አዳምጠኝማ ! !🌸🌸🌸

መቼም ከሙዝ የብርትኳን ጣዕም አይጠበቅም! ከተስፋ መቁረጥም ሞት እንጂ ምንም የለም ፡፡ በዚህ ሳምንት ብቻ በፌስቡክ የማውቃቸውን ከ፰ ሰዎች አገኘሁ ሁሉም ተስፋ ቆርጠናል መሞት ብቻ ነው የሚታየን ያሉኝ ነበሩ ! ! የሚገርመኝ ነገር መሞት ቀላል ነው እኮ ፡፡ መኖር ግን ዋጋ ያስከፍላል ፡፡

ፈጣሪህ የሰጠህን ቀን ተስፋ አድርገህ ኑር ሁሉም ሰው ይኑር ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ ፡፡ ወዳጄ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል ፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ ፡፡ በነገሮች አትረበሽ ፡፡ አየህ አንፖል ተቃጠለ ተብሎ ቤት አይቀየርም ፡፡ አንፖል ተቃጥሏል ብሎ ቤት የሚቀይር ሞኝ ነው ፡፡ አንተም አንዱ የህይወቴ ጉዳይ አልተሳካም ብለህ ራስህን አታጥፋ ፡፡ ይልቅስ አምፖልህን ቀይር ችግርህን ተጋፈጠው ፡፡ ጭንቀትህን አስጨንቀው ፡፡

ካህሊል ጅብራል እንዲህ ይላል ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው ፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል ፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው ፡፡

በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ህይወትህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም ፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ነው ፡፡ “መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው ።” በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው ። የምን ተስፋ መቁረጥ……. !


ፌስቡክን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም ፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና ፡፡


ስለዚህ አንተም ይህ አሁን ያነበብከው ፅሁፍ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ካገኘሀው የእርስዎ ዘመዶችህ እንዲያነቡትና ትምህርት እንዲወስዱ ዘንድ ሼር ያድርጉላቸው ። ቻናሌንም Join አድርገው ይቀላቀሉኝ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *